Saturday, July 18, 2015

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የዘፈቀደ እስር እና ጎጂ አያያዝ!!



   በአሁኑ ግዜ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ተሳትፎ ውስጥ አዲስ መጭ የሆኑ ፓርቲዎች የተሳተፉበት እንቅስቃሴ መካሄዱን ይታወቃል፣ ምናልባት ካለፉት የምርጫና የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችም በትንሹም   ቢሆን ልዩ ያደርጓል፣  በዚህ ሁኔታ    ስጋት ላይ የወደቀው የኢህአዴግ ስርዓት በጸጥታ ሃይሎቹ አማካኝነት የተቃዋሚ ድርጅቶችን ፅ/ቤት ሰላም በማደፍረስና በጽህፈት ቤቱ ውስጥ የሚሰሩ አባላት በማሰራቸውና የፓርቲዎችን ንብረቶች በመውረሳቸው ምክንያት ተቓዋሚዎች መንግስትን ተቃውሞው ሊያደርጉት ያሰቡትን ሰላማዊ ሰልፎች ሳይካሄዱ ተሰናክለው ቀርቷል።
   
  አንዳንድ በህዝቡ ትልቅ ተቀባይነት የነበራቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች  ሰላማዊ ሰልፉን ለማካሄድ ለመንግስት ፈቃድ አቅርበው የነበረው ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱና በፓርቲውቹ አባላትና  ደጋፊዎች ላይ ይደርስ የነበረው ዛቻ፤ ማስፈራራትና ለመንግስት ስጋት ይሆናሉ የተባሉትን ግለሰዎች ወደ እስር ቤቱ የማጎር ሁኔታ እጅግ ከፍተኛ እንደነበር ሁሉም የአገራችን ህዝብ በቅርብ የተከታተለው መሆኑን ይታወቃል።

    በአገራችን ውስጥ የዘፈቀደ እስር እና በእስር ቤቶች የሚደረግ ጎጂ አያያዝ ከፍተኛ ችግር መሆኑን ቀጥሏል ተማሪዎች፤ የተቃዋሚ ጎራ አባላት፤ ጋዜጠኞች፤ የሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎች እና ሌሎችም የመሰብሰብ፤ ሃሳብን የመግለጽ’ና የመደራጀት መብታቸውን መግለጽ የሚፈልጉ ሰዎች በየጊዜው እየታሰሩና መብታቸው እየተረገጠ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው።

    አብዛኛውን ጊዜ በፖለቲካ ምክንያት በሚያዙ ሰዎች ላይ በተለይም ተከሳሾቹ ከፍርድ ሂደት በፊት በሚታሰሩበት ግዜ በተለያዩ  የአገራችን  እስር ቤቶችና  በተለይም ቃሊቲ ተብሎ በሚታወቀው አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራን ክልኦት ዘይፍለጡ አብያተ ማእሰርትን  አጅግ አስቃቂ በሆነ መንገድ ግፍ እየተፈፀመ እንደሆነ ይታወቃል።

    በተለያየ ምክያት የተለያዩ ሰዎች በላያቸው ላይ ክስ ከመመስረቱ በፊት ብዙ ጊዜ የህግ አማካሪ እንዳያገኙ እንደሚደረግና ያልተገባ አያያዝ የተፈጸመባቸው እስረኞች ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ከፍርድ ቤቶች ምንም አይነት መፍትሄ እንደማያገኙና እስር ቤቶቹና ሌሎች የማቆያ ቦታዎች በገለልተኛ ታዛቢዎች በመደበኛነት እንዲጎበኙ የማድረጉ ሁኔታ የሚታሰብ አይደለም።
  
    ስርዓቱ እንደ መነገጃ የሚጠቀምበት ከመንግስት ጋር ቀረቤታ ያለው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የተወሰኑ እስረኞችን’ና እስር ቤቶችን ሁኔታቸውን እየተከታተልኩት ነኝ ቢልም ሃቁ ግን ስርዓቱ ዴሞክራሲያዊ እንደሆነ ለማስመሰል እንጂ ተከታታይ የሆነ ክትትልና የምርመራ ስራዎች አካሂዶ አያውቅም።
     ወደ አገራችን ተጉዞ የነበረው የአውሮፓ ፓርላማ የልዑካን ቡድን አባላት አስቀድሞ ፈቃድ ተሰጥቶአቸው የነበረ ቢሆንም አዲስ አበባ የሚገኘውን የቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንኳን እንዳይጎበኙት መደረጉ  አንዱ ማሳያ ነው።
  
   ባጠቃላይ በአገራችን ውስጥ ያለው የሰብአዊ መብት አያያዝና የእስር ሁኔታ መንግስት እንደሚለው ማለት የፖለቲካ እስረኞችና ሌሎች የህግ ታሳሪዎች ህገ መንግስቱ እንደሚያስቀምጠውና ህጉ በሚፈቅደው ሁኔታ የሚፈጸም ሳይሆን ስርዓቱ ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት በማያያዝ ያለ ምንም ማጣራት የሃሰት ውንጀላ በመለጠፍ  በንፁኃን ዜጎቻችን ላይ የዘፈቀደ እስርና ጎጂ የሆነ እያያዝ እየፈፀመ ይገኛል።