በደረሰን መረጃ መሰረት በማእከላዊ እዝ የሚገኙ
ወታደሮች በአመታዊ ግምገማ ላይ ያለ አግባብ የመንግስት ስም ታጠፋላችሁ፤ የተቃዋሚ ሃይሎችን አስተሳሰብ ትደግፋላችሁ በሚልና በመሳሰሉት
የግምገማ ነጥቦች የተነሳ በዚህ ሳምንት ከእዙ ወደ 63 ወታደሮች መጥፋታቸውን ተከትሎ ከኃይል አመራር በላይ በስብሰባ መጠመዳቸው ታውቋል።
ይህ በንዲህ እንዳለ በአሁኑ ሰአት ሰራዊቱ ለምን አታሰናብቱንም በሚል
ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርብም መልስ እንዳልተሰጠውና አነሳሽ ተብሎ እየታሰረ መሆኑን የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል።