Saturday, August 22, 2015

የዓዲ ግራት ነዋሪዎች የማንነት ካርድ በሚያወጡበት ሰዓት 250 ብር እንዲከፍሉ እየተገደዱ በመሆናቸው ምሬታቸውን በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ።



    በምጮቻችን መረጃ መሰረት የዓዲግራት ነዋሪዎች የማንነት ካርድ ለማውጣት በሚፈልጉበት ሰዓት በከተማው አስተዳዳሪዎች ከ250 ብር በላይ እንዲከፍሉ እንደሚገደዱ የገለጸው መረጃው ይህን ጉዳይ ከድሃው ህብረተሰብ አቅም የማይመጣጠን መሆኑን ታይቶ መፍትሄ እንዲደረግላቸው ጠይቀው አወንታዊ መልስ እንዳላገኙና ምሬታቸውን በማቅረብ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
    የአዲ ግራት ከተማና አካባቢው ከፍተኛ የጸጥታ ችግር እንዳለበት የገለጸው መረጃው ነዋሪው ሕብረተሰብ ከቦታ ወደ ቦታ በሚንቀሳቀስበት ግዜ በካድሬዎችና በሚልሻዎች እየተፈተሸና እየተስፈራራ መሆኑና የማንነት ካርድ ለማውጣት በሚፈልግበት ግዜ ደግሞ ከዓቅሙ በላይ ገንዘብ ስለሚጠየቅ ነዋሪው ህብረተሰብ በስርዓቱ ላይ ተቃውሞ እያሰማ እንደሚገኝ ታውቋል።