Thursday, August 20, 2015

የትግራይ ምእራባዊ ዞን አስተዳዳሪ የሆነው ፍስሃ በርሀ ከ44 ሚልዮን ብር በላይ ለግል ጥቅሙ በማዋሉ የተነሳ የዞኑ ነዋሪዎች ምሬታቸውን በማሰማት ላይ መሆናቸው ተገለፀ።



    በመረጃው መሰረት የምእራብ ትግራይ ዞን አስተዳዳሪ የሆነው ፍስሃ በርሀ ለሁመራ ከተማ መሰረተ ልማት ተብሎ በተለያየ መልኩ ከህዝብ የተዋጣው 44 ሚሊዮን ብር ስልጣኑን ተገን በማድረግ ለግል ጥቅሙ ማዋሉን ታውቆ እያለ እስከ አሁን ድረስ ሊጠየቅ አልቻለም በሚል የሁመራ ከተማ ከንቲባ አቶ አለሙ አየነው ይመራው በነበረው ስብሰባ ላይ ጉዳዩ ቢነሳም አጥጋቢ የሆነ ምላሽ እንዳልተሰጠበት ለማወቅ ተችሏል።
   መረጃው በማከል ይህ በትክክል የተመደበውን በጀት ያጠፋፋው ፍስሃ በርሀ እንደሆነ አስቀድሞ በማስረጃ አስደግፈው ቢያቀርቡም የተጠፋፋው ገንዘብም የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት እጅ ሰላለበት ገንዘቡን ያጠፋፋው ሃላፊ አንድ ጊዜ ወደ ሌላ ስራ ሄደዋል። ሌላ ጊዜ ደግሞ ታምመዋል በማለት እርስ በርሳቸው የሚጋጩ ምክንያቶችን በመደርደር እስከ አሁን ድረስ ወደ ህግ ሊቀርብ ባለመቻሉ ምክንያት ነዋሪውን ህዝብ እንዳስቆጣው መረጃው አስረድቷል።