Thursday, August 20, 2015

በሁመራ ከተማ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች እርስ በራስቸው በጥቅም ተሳስረው የህዝብና የሃገርን ገንዘብ በማጠፋፋት ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ።



በትግራይ ምእራባዊ ዞን ሁመራ ከተማ ውስጥ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች እርሰ በራሳቸው በጥቅም ተሳስረው የህዝብና የሃገርን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት እንደሚገኙ የገለፀው መረጃው ከነዚህም አንዱ የከተማዋ የፀጥታ ሃላፊ የሆነው በሪሁ የተባለ ከነ ግብረ አበረቹ ጋር በመሆን 150 ሺ ብር እንዳጠፋፋ በምክር ቤቱ ተረጋግጦ እያለ ጉዳዩን ከተጣራ ምስጢራቸው እንዳይወጣ የሰጉት አመራሮቹ ተሯሩጠው በዋስ እንዲለቀቅ በማድረግ ከአካባቢው እንዲጠፋ ማድረጋቸው ለማወቅ ተችኋል።
     በተመሳሳይም በሁመራ ከተማ የቴሌኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ሰራተኞች በስርአቱ ላይ ያላቸውን እምነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነስ በመሄዱ ምክንያት ጀማል የተባለ የድርጅቱ ሰራተኛ ከ100,000ሺ ብር በላይ ገንዘብ ይዞ ሃምሌ 26 2007ዓ/ም  መጥፋቱን መረጃው አክሎ ገልፀዋል።