Thursday, August 20, 2015

የዓድዋ ከተማ ነዋሪዎች በመኖሪያ ቤት እጥረት ምክንያት መቸገራቸው ምንጮቻችን ከአካባቢው ገለጹ።



    በመረጃው መሰረት በትግራይ ማእከላዊ ዞን የዓድዋ ከተማ ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት እጥረት በማህበራዊ ኑሮአቸው ላይ ከፍተኛ ችግር መፍጠሩን የገለፀው መረጃው ችግሩን እንዲፈታላቸው በማለት በተደጋጋሚ ለሚመለከታቸው አካላት ሲያቀርቡት የቆዩት ጥያቄ እስካሁን ድረስ ከቃል ያለፈ ምንም አይነት መፍትሄ ማግኘት እንዳልቻሉ ለማወቅ አችሏል።
    የከተማዋ ነዋሪዎች ብሶታቸውን እየገለፁ ባሉበት በአሁኑ ግዜ የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ለማስመሰል ሲሉ የህወሃት ጉባኤ ካለፈ በኋላ መፍትሄ ይደረግላችኋል ብለው ሊያታልሏቸው ቢሞኩሩም ህዝቡ ግን በርካታ ጉባኤዎች አሳልፋችኋል ቢሆንም ግን ከቃል ባለፈ ያገኘነው መፍትሄ የለም በማለት ሃሳባቸውን እንደተቃወመው መረጃው አክሎ አስታውቋል።