Friday, October 30, 2015

በዚህ ሳምንት አምባገነኑ የኢህአዴግ ስርአትን በመቃወም በርከት ያሉት ወጣቶች ወደ ትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( ትህዴን) ማሰልጠኛ ማእከል እንደተቀላቀሉ ተገለፀ፣ ከተቀላቀሉ ወጣቶች ለመጥቀስ ያህል፦



1. መሰለ ሰረቀ ከትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ታህታይ አድያቦ ማይ ኹሕሊ ቀበሌ
2. ላይን ፍስሃ ከሰሜናዊ ምእራብ ዞን ሸራሮ ከተማ ሙሴ ቀበሌ
3. ፅጌ ሚካኤል ከማእከላዊ ዞን አሕፈሮም ወረዳ ገርሁ ሰርናይ ቀበሌ
4. ጎይትኦም ዕሉም ከሰሜናዊ ምእራብ ዞን አስገደ ፅምብላ ህንፀት ቀበሌ
5. ሓጎስ ቢሆን ከማእከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ ደብረ ሓርማዝ ቀበሌ
6. ጉዕሽ አስሊ ከማእከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ ማይ ዓይኒ ቀበሌ
7. ደሳለ ወላይ ከምስራቃዊ ዞን ኢሮብ ወረዳ እንዳልጌዳ ቀበሌ
8. ሓለፎም ገብረህላሰ ከማእከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ ማይ ወዲ ዓምበራይ ቀበሌ
9. ሃይለስላሴ ገብረ አነኒያ ከምስራቃዊ ዞን ሳዕስዕ ፃዕዳ እምባ ወረዳ ፍረወይኒ ቀበሌ
10. አብርሃም መድሃኒየ ከማእከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ ብርሽዋ ቀበሌ
11. ወታደር ተገኝ መሰሉ ከ31ኛ ክፍለ ጦር 9ኛ ረጅመንት አንደኛ ሃይል (መድፈኛ የነበረ ) ከብሄር አማራ
12. ወታደር አርኣያ ኪዳነ ከ25 ክፍለ ጦር 1ኛ ረጅመንት 5ኛ ሃይል 2ኛ ጋንታ ከብሄር ትግራይ የሚገኙባቸው ሲሆኑ። በስልጣን ላይ ያለው ገዢው የኢህአዴግ ስርአት እየተከተለው ባለ ብልሹ አሰራር በመቃወም የራሳቸውና የህዝባቸውን ችግር በትጥቅ ትግል ለመፍታት ወደ ትህዴን እንደገቡ ገልፆዋል፣
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ወጣቶች በአንድ ላይ በሰጡት መረጃ መሰረት። ወጣት ዜጋ በአገሩ ሆኖ ሰርቶ ኑሮውን የሚያሻሽልበት እድል ባለመኖሩ የተነሳ። ስራ ለመፈለግ ወደ ሁመራ በሚሄዱበት ጊዜ የአካባቢውን የእርሻ መሬት ደርቆ ለሁለተኛ ጊዜ በመታረሱ ወደ ቦታቸው ለመመልስ ፍልገዉ ለትራንስፖር የሚሆን ገንዘብ በማጣታቸው የተነሳ በየ በርሃ ለመንከራተት እንደተጋለጡ ኣስድትዋል፣