Friday, October 30, 2015

በመረብ ለኸ ወረዳ የሚኖር ህዝብ ታራሽ መሬት የሚመለከት ጥያቄ ያለው ሲሆን ለዚህ ለመፍታት በሚል አስተዳደሮች እየተከተሉት ያሉት ፍትሃዊነት የጎደለው የመሬት አሰጣጥ ዘዴ እንደሆነ ተገለፀ።



በመረጃው መሰረት በየክልሉ ቀን በቀን ህብረተሰቡ የፈፀመው ወንጀል ሳይኖሮው የአይኑን ቀለም አላማረንም እየተባለ በኢህ አዴግ ካድሬዎች ትእዛዝ እየታሰረና እየተሰቃየ ያለው ዜጋ ከመብዛቱ የተነሳ ይህንን ያህል ነው ለማለት አስጨጋሪ እንደሆነ ከገለፀ በኃላ እንደዚህ ያለ ሁኔታ ሁነህ የባንዴራና የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ማክበር የማስመሰል ተግባር ከመሆኑ በስተቀር መሬት ላይ የሚወርድ ትርጉም እንደሌለው ለማወቅ ተችሏል።
      መረጃው በማከል የአገራችን እስር ቤቶች በአሁኑ ጊዜ በነዚህ አምራች ወጣቶችና ዜጎች አጥለቀለቀው ያሉት ወንጀል ፈፅመው በፍርድ ቤት የተፈረደባቸው ሳይሆኑ በፖለቲካ አወሳሰንና አግባብነት በሌለው ለአመታት ያህል መታሰራቸውና መሰቃየታቸው ንፁኃን ዜጎች በአገራቸው ክብር አጥተው ወደ ባእድ አገር ፊታቸው እንዲያዞሩና ከአገር ከወጡ በኃላም ሱር ነቀል የሆነ የስርአት ለውጥ ሳይደረግ ወደ አገራቸው ለመመለስ ፍቃደኞች ያልሆኑ ዜጎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው በመጨመር ላይ እንደሚገኙ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።