Friday, November 27, 2015

የመሬትን ችግር በማንሳት የህዝብን ተጠቃሚነት አይረጋገጥም!!



መሬት ሲባል በአንድ አገር የሚገኝ ህብረተሰብ መኖሪያውንና መቀበሪያውን ስለሆነ ህዝብ በእኩልነት እንዲዳረሰው በክንክን ልይዘውና ሊጠብቀው የግድ ነው፣ ሰለ ሆነም ቀደምት ወላጆቻችን የአገራችን መሬትና የተፈጥሮ ሃብቶቻችን ለመቀማት ተንደርድረው የመጡት የባእድ ሃይሎች በፅናት ተጋፍጠው አሸንፈው ዛሬ ደረታችን ነፍተን እንድንናገር ታሪክ አውርሰውን አልፈዋል።
  ይሁን እንጂ በየጊዜው የነበሩትና ያሉትን የአገራችን መሪዎች መሬት ለህዝብ ለማዳረስ ይሁን ባለቤትነትን ለማረጋገጥ የሚከተሉት አሰራር ሲታይ ፍትህ ያጣ ያደረ በሽታ ሆኖ ቆይተዋል።
  ይህ ማለት ደግሞ በአገራችን ከመሬት የበለጠ ሃብት ካለመኖሩ የተነሳ ለአገራችን ኢኮኖሚም መሬት ስለ ሚሰከመው በየወቅቱ ስልጣን ላይ የሚመጡ መሪዎች መሬቱን በእጅ ቁጥጥራቸው ስር በማድረግ አማራጭ የሌለው የፖለቲካ መሳሪያ አድርገዉት ቆይተዋል።
  በውጤቱም መሬት የሁሉም ዜጋ መሆን ሲገባው በጥቂቶች ባለ ስልጣኖችና ጋሻ ጃግሬዎቻቸው እንዲውል በማድረግ ድሃ መሬት እንደማይ መለከተው ተቆጥሮ አገልጋይና የበይ ተመልካች ሆኖ እንዲሄድ የፈረዱት ህዝብ የስርአቱን አሰራር በመቃወም ጥቅሞቹንና የመሬት ባለቤትነቱን በማረጋገጥ የድርሻውን ለመረከብ ያለፉትን ሁለት ተከታታይ ስርአቶች በትግሉ ነቅሎ ቢጥላቸውም በህዝቡን ትግል ወደ ስልጣን የመጣ  ኢህአዴግም በባሰ መልኩ ቀጥሎበታል።
  በስልጣን ላይ ያለው ስርአት ካለፉት ስር አቶች አስተካክያሎህ ብሎ በህገ መንግስ ላይ ያፀደቀው የከተማና ገጠር መሬት የተፈጥሮ ሃብቶች  የሚመለከት በህዝብ  በመንግስት ስም በማለት ያሰፈረው ህግ በተግባራዊነቱ ላይ ህዝቡን ሲያየው ለሙስናና ለቡሉሹ አሰራር የተጋለጠ ሆኖ ነው የምናገኘው።
  በየጊዜው የሚያወጣቸው የመሬት አዋጆችና አፈፃፀማቸው ቢሆንም የህዝቡን ችግር ሊቀርፉ ታስቦ ሳይሆን ለስርአቱ ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ሆን ተብሎ የወጣ በመሆኑ ችግሩን ከነበረበት በባሰ መልኩ እንዲሄድ አድርገዉታል።
  በዚህም መሰረት በሁሉም የአገራችን አካባቢዎች የሚገኝ ህዝብ ስለ እድገቱንና ንሮውን ሲፈተሽ በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ ስለ መሬት ነው የምናነሳው፣ አንድ የአገራችን አርሶ አደር የመሬት ይዘቱ  በመካከለኛ የያዘው ሲገመገም የመሬት ስፋቱ አንድ ሄክታር አይደርስም፣ ከዚህ ባለፈም ለአቅመ አዳም የደረሰው ወጣት ዜጋ ሊያገኘው የሚገባው ህገ መንግስታዊ መብቱ በማጣቱ የተነሳ ጥበት ባለው መሬት ላይ  አምስትና ስድስት ቤተሰቦች በአንድ ላይ ታጉረው እንዲኖሩ ተገደዋል።
በአገራችን የጠራ የመሬት ፖሊሲ ባለ መኖሩ የተነሳ የኢህአዴግ መሪዎች ሁሉም በእጃቸው በማስገባት እንደፍላጎታቸው ሊሸጡት ከህዝብ እየቀሙ ለባለሃብቶች ሲሰጧቸው እየታዘብን ነን፣ በአገራችን እየታየ ያለው የኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግሮች ዋነኛ መንስኤዎች ከመሬት አስተዳደር በተሳሰረ ብልሹ አሰራር ነው።
 መሬትን ሊያስተዳድሩ ተብለው በየአካባቢው ተሽሞው የሚገኙ የመሬት ዴስክ ወረዳና ቀበሌን ብሎም ቀጠና እንኳን በአግባቡ ሊያስተዳድሩና ሊያገለግሉ ይቅርና መሬት ያለ ህጋዊ ሲወረር እንዳላዩ ሲክዱ፤ የህዝቡ ከፍተኛ አቤቱታዎች ቀልጣፋ ምላሽ የሚሰጡ ሳይሆኑ። ጉቦ የሚጠብቁ በመሆናቸው ጉቦ ላልሰጣቸው ድሃውን ህብረተሰብ ደግሞ እድሉን እያማረረ እንዲመላለስ እያደረጉት ይገኛሉ።
በአገራችን እየታየ ያለው ቅጥ ያጣ የመሬት አስተዳደር ብቻ ሳይሆን በዚህ የተነሳ የስራ አጥነትና የዜጎች ነፃነት፤ ክብርና ዴሞክራሲያዊ መብቶችም እየተጣሱ የሚያየው ያጣ ህዝብ ሆኖ እንዳለ ከማንኛውም ዜጋ የተደበቀ አይደለም።
 ይህንን እያወቁ ወደ ገደል አፋፍ ላይ እየመሩት የቆዩት የኢህአዴግ መሪዎች ለዚህ ተከስቶ ያለው የማህበራዊ ጉስቅልናና ያለመረጋጋት በዚህ ሳምንት የስር አቱ ጠቅላይ ሚኒስተር የመራው የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማእከል በሚል የይስሙላ መድረክ ባካሄደው ጊዜ በነሱ ምክንያት የተከሰቱትን የህዝብ ችግሮች በመጥቀስ ሲዘባርቁ ታይተዋል።
ዩን እንጂ የኢህአዴግ መሪዎች ለነዚህ መሰረታዊ የሆኑት የመሬት አስተዳደር ጥያቄዎችን በሰከነ መንፈስ አዳምጠው በቅን ልቦና ለመመለስ የሚያስችላቸው የሞራል ብቃት መኖርና ያለመኖር ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊ ባህላቸው ጭምር አይፈቅድላቸውም።
ምክንያቱም የችግሩ መንሲኤዎች ራሳቸው በሚከተሉት ቀና ያልሆነ ፖሊሲና የመሬት አስተዳደር በመሆኑ መሰረታዊ ጥቅማቸው የሚነካ በመሆኑ የመፍትሄ አካል ሊሆኑ አይችሉም ሰለዚህ የመሬት አስተዳደር ችግር በመጥራት የህዝቡን ተጠቃሚነት ፈፅሞ አይረጋገጥም።