Saturday, January 2, 2016

በትግራይ ክልል የሚካሄድ የውጤት ተኮር ግምገማ ለስርአቱ የፖለቲካ መሳርያ ፍጆታ እየዋለ መሆኑ ምንጮቻችን የላኩት መረጃ አመለከተ።



   በትግራይ ክልል የሚገኙ የመንግስት  ሰራተኞች  በውጤት ተኮር ገምገማ ሊያልፉ ከሆነ የስርአቱ ደጋፊንና አባል እንዲሆኑ በመገደድ ላይ መሆናቸወን የገለፀው መረጃው፣ በዚህ ፍቃደኛ ያልሆኑት ደግሞ የሚሰጣቸው ነጥብ ትንሽ በመሆኑ በተለያዩ የስራ እድገቶች እንዳማይሳተፉና  በተለይ ደግሞ በትምህርት ሚኒስተር አንድ መምህር የሚለካው በስራው ሳይሆን ለፖለቲካ ፍጆታ እየተባለ የስርአቱ አባል ለመሆን ሰለሚገደድ  በትምህርት ጥራት ላይ እንቅፋት በመፍጠር ላይ መሆኑ ተገለፀ።
 
   መረጃው ጨምሮ በሳዕሲዕ ፃዕዳ እምባ ወረዳ የሚገኙ አስተማሪዎች ገንዘባቸውን ከፍለውና ደክመው በትምህርታቸው ማሻሻያ ቢያደርጉም የደመውዝ ጭማሪና የተለያየ ጥቅማ ጥቅሞች ስለማያገኙ የሚሰሩት ስራና የሚካፈላቸው ደመወዝ ተመጣጣኝ ባለመሆኑ በላያቸው ላይ የሞራል ወድቀት እንደፈጠረባቸው ለተጎጂ አስተማሪዎች  መሰረት በማድረግ ምንጮቻችን ከአከባቢው ገለፁ።