Saturday, January 2, 2016

በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሰው ኦፌኮ እየተካሄደ ባለዉን የህዝብ ተቃውሞ ጋር በተሳሰረ ምክንያት ከፍተኛ አመራሮቹና 500 አባላቱን እንደታሰሩበት ተገለፀ።



   በመረጃው መሰረት የኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ ድርጀት/ኦፌኮ/ ከ6 ከፍተኛ አመራሮቹ  ጨምሮ 500 የድርጅቱ አባላት  በዚህ ሳምንት መታሰራቸውና ከታሰሩት ከፍተኛ አመራሮቹ  ጥቂቶቹ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር ጉርሜሳ አያኖ ፤ የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ፣ አዲሱ ቡላላ፤የድርጅቱ  ስራ አስከያጅ  ደረጀ መርጋ ፤የድርጅቱ  ፀሓፊ መምህር አለሙ ኣብዲሳ።የድርጅቱ ኦዲተር፣ መምህር ታሪኩ፤ የድርጅቱም ክትል ፀሓፊ፣ ደጀኔ ጣፋ ፤ የድርጅቱ ምክትል ዋና ፀሓፊና በቀለ ጉርባ የሚገኝባቸው በስርአቱ ፖሊሶች ተይዘው እንደታሰሩ ለማወቅ ተችሏል።
   መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው  ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት ከፍተኛ አመራሮች በተጨማሪ በየዞኖቹ የሚገኙ የድርጅቱ አመራሮችም እንደታሰሩና ከእነሱም የተወሰኑትን ስማቸው ለመጥቀስ የወለጋ ዞን አመራር መሰረት ዳቦ፤የምስራቅ አሩሲ አመራር አህመድ ኢቦ፤ የባሌ አመራር ሁሴን አምዳ ፤የሆሮ ጉድሮ አመራር ደገባስ ዋቀዩ፤ የኢሊባቡር አመራር እስማኢል ሑሴንና ያዛቸው  አብዲሳ በኢሉባቡር  በፖሊስ ተይዘው በእስር ቤት እንደሚገኙ ታወቀ።
   በመጨረሻም የወረዳው አመራርና  አባላት ጭምር 500 የሚደርሱ የድርጅቱ ኣባላቶች በተለያዩ አከባቢዎች እንደታሰሩና በአጠቃላይ በተነሳው ተቓውሞ ምክንያት ከ4000 በላይ ህዝብ የታሰረ መኖሩን ተገለፀ።
  ይህ በእንዲህ  እንዳለ ከ300  በላይ ንፁሃን ወገኖቻችን  የገቡበት እንዳልታወቀና፣ 1500 የሚደርሱ ዜጎች  ደግሞ በከባድ ተጎድተው በወሊሶ ሉቃስ ፤በቅዱስ ጳውሎስ ፤በሚኒልክና ጥቁር ኣንበሳ ሆስፒታሎች ገብተው በመታከም ላይ መሆናቸወን  ምንጮቻችን አስረድተዋል።