Saturday, January 2, 2016

የኢህኣዴግ ገዢው ስርአት በጋዜጤኞች ላይ እየወሰደው የሚገኝ የማሰር እርምጃ የሲፒጀይ ተቓም ኮምቴ በዚህ ሳምንት ባወጣው መግለጫ ወቀሰ።




    ባገኘነው መረጃ መሰረት የኢህኣዴግ ገዢው ቡድን ያላቸው የስራ ሞያ አዉቆው ኃላፍነታቸው በተዋጡ ጋዜጠኞች ላይ እየፈፀመው የሚገኝ የማሰር ተግባር የመረመረ የሲፒጀይ ድርጅት ኮሚቴ የቴሌቭዥን ጣብያ አዘጋጅ፣ ኦሮምያ ፍቃዱ ሚርካንና የነገረ ኢትዮጵያ ድረገፅ ዋና አዘጋጅ ጌታቸው ሽፈራዉን በዚህ ሳምንት የታሰሩበት ምክንያት ህጋዊ አይደለም ብሎ እንደኮነነው ተገለፀ።

     ይህ አለማዊ የጋዜጠኞች የሰብአዊ መብት ተማጓች ድርጅት ኮምቴ በመግለጫው ጨምሮ እንዳስቀመጠው በኢትዮጵያ የሚገኝ መንግስት ጋዜጠኞች ማሰርና ህዝብ መረጃ የማግኘት መብት የማፈን ተግባር እንድያቆም ካስታወቀ በኃላ፣ በአሕፅሮት የሲፒጀይ ድርጅት ተብሎ የሚጠራ ኮምቴ ጨምሮ፣ የኢትዮጵያ መንግስት በአንድ ሳምንት ዉስጥ ሁለት ጋዜጠኞች አስረዋል የተሳሩበት ምክንይት ደግሞ ግለፅ አይደለም ይህ ደግሞ የአለም ሕግ መጣስ ነው በማለት ለኢህአዴግ ስርአት ኢ-ዴሞክራስያዊ አስራር በግልፅ እንደተቃወመው ለማወቅ ተችለዋል።