Sunday, January 31, 2016

በአዲስ አበባ የተጀመረውን የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ተከትሎ ኢህአዴግ የፀጥታ ሰጋት ሰላደረው፣ በመኪና አከራዮች ላይ ተፅእኖ ሲያሳደር እንደሰነበተ ታወቀ።



         ባገኘነው መረጃው መሰረት፣ በአዲስ አበባ ሲካሄድ የሰነብተው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ በኢትዮጵያ ላይ አጋጥሞ ባለው ተቃውሞ ጋር ተያይዞ፣ የፀጥታ ስጋት ሰለፈጠረ ኢህአዴግ ለደህንነት በሚል ሽፋን የመኪና አከራዮች የሆኑት ማህበራት፣ ለማን ማከራየት እንዳለባቸው የተሟላ መረጃ እንዲኖራቸው በሚል ሽፋን ጥብቅ መምሪያ ያስተላለፈ ሲሆን፣ መምሪያውን የማይተገብር አከራይ ደግሞ ከባድ ቅጣት እንደሚወሰድበት የማስጠንቀቂያ መምሪያ እንዳስተላለፈ መረጃው አስረድቷል።

        በዚህ ሳምንት የደርጅቱ የደህንነት ሃላፊዎች መኪና የሚያከራዩ  በመጥራት፣ ኮድ 2 የሆነ የግል ሰሌዳ የተለጠፈባቸው ተሽከርካሪዎች ብቻ ለክራይ እደሚያቀርቡ መምሪያ የተሰጣቸው ሲሆን፣ የመኪና አከራዮች የግል ድርጅቶች ደግሞ መምሪያውን እንዳልተቀበሉት መረጃው አክሎ ገልፀዋል።


No comments:

Post a Comment