Sunday, October 12, 2014

በአማራ ክልል የሚገኙ የኢህአዴግ ካድሬዎች ስራ ፈላጊ ለሆኑ ዜጎቻችን ወደ ትግራይ ክልል ሁመራ አካባቢ ሄደው እንዳይሰሩ መከልከላቸው ተገለፀ፣





እነዚህ በአማራ ክልል የሚገኙ የብአዴን-ኢህአዴግ ባለስልጣኖች፤ በትግራይና በአማራ ህዝብ መካከል መቀራረብ እንዳይኖር ተንኮሎችን እያበጁ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው፤ በሁለቱም ክልሎች የመሬት ቅርምት ጠብ በመነሳቱ ምክንያት፤ ስራ ለሚፈልጉ ዜጎቻችን ወደ ሁመራ ከተማ እንዳትሄዱ፤ መተማና አብደልራፍዕ ሄዳችሁ ስሩ በማለት እየቀሰቀሷቸው መሆናቸውን  ምንጮቻችን ከአከባቢው አስረድቷል፣
    መረጃው በማስከተል የአማራ ክልል ህዝብ በካድሬዎቹ የቀረበውን ሃሳብ ሳይቀበል የትግራይ ህዝብ የበደለን ነገር የለም፤ እኛ የአንድ አገር  ሰዎች ነን አትለያዩን፤ ችግር ካላችሁ እራሳችሁ ፍቱት፤ በእንዲህ አይነት ከፋፋይ ፖሊሳችሁ ህዝቡን አታጣሉት በማለት ሑመራ አካባቢ በመሄድ ስራቸውን እያከናወኑ መሆናቸውን መረጃው ጨምሮ አመልክቷል፣