Wednesday, October 12, 2016

የዜጎች እልቂት ለማብረድ ሁሉም አይነት ትግል እናጠናክር!!



    የአገራችን ቢሄር ቢሄረ ሰዎች ቆሞ ከበሰበሰው ኣምባገነናዊ ስርአት ለማላቀቅ እየተደረገ ከሚገኘው ሁለ ገብ ትግል ሌት ተቀን ተጠምደው ከባድ ዋጋ በመክፈል ላይ ይገኛሉ፣
    ይህ ፀረ ህዝብ ስርአት ከህዝብ ፍላጎት ዉጭ በሃይል የህዝብ ደም እየመጠጠ በስልጣን ለመኖር እያካሄዳቸው የቆየና ያለ ሁሉም አይነት እንቅስቃሴ እየተጋለጡ መጥተዋል። የአገራችን ህዝቦች ሰላም ፍትሕ ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር እንዲያገኙ ለአመታት ጠብቀው መፍትሔ ባጡበት ወቅት ህገ መንግስታዊ መብታቸው ተጠቅመው በአደባባይ ወጥተው ድምፃቸው ከፍ አድረገው እንዳያሰሙ ሁሉም አይነት መንገድ የሰላማዊ ትግል  ተዘግተዋል፣
      በመሆኑም ደግሞ ህዝባችን ለ25 አመታትን የሚያህል በላዩ ላይ ሲወርደው የቆየና ያለ የተለያዩ ግፎች ለአንዴና ለመጨረሻ በትግሉ እንዲያበቃ አንፃር ጠላቶቹ እያካሄደው የሚገኘው የእምቢ አልገዛም ተቃዉሞዎችን ስርአቱ መፍትሔ ከመስጠት ይልቅ የፀጥታ ሃይሎች እያሰማራ በንፁሃን ዜጎቻችን ላይ የእሩምታ ጥይት በመቶከስ በማሃል ጓዳና ደማቸው ደመ ክልብ ሆኖ እንዲቀር እያደረገ ነው፣
   በመሆኑም ደግሞ ህዝባችን ለ 25 አመታትን የሚያህል በላዩ ላይ ሲወርድበት የቆየና የለ መቓጫ ያልተገኘለት ግፍ ለአንዴና ለመጨረሻ በትግሉ እንዲያበቃ የበዳየቹ አንፃር እያካሄደው ባለ የእምቢ አልገዛም ተቃዉሞዎችን ተገቢ መፍትሔ ከመስጠት ይልቅ የፀጥታ ሃይሎች እያዋፈረ በንፁሃን ዜጎቻችን ላይ የጥይት እሩምታ በመተኮስ በማሀል ጎዳና ደማቸው ደመ ከልብ ሆና እንዲቀር በየቀኑ እየሰራ ይገኛል።
  የዚህ ምሳሌ ስናይ የሩቅ አስቆይተን ባለፈው አመትና አሁን ብቻ በተወሰነ መልኩ መጥቀስ ይቻላል። በዚህ መሰረት ደግሞ የኢህአዴግ ፀረ ህዝብ ስርአት እንደልማዱ ከሚፈራው የህዝብ ማነቆ ለመላቀቅ  ያደረገው የመልካም አስተዳደር  ሴራ ሳይጀምር በሕዳር ወር በማስተር ፕላን ምክንያት በኦሮሞ ህዝብ የተነሳው ህዝባዊ እምቢተኝነት ተቀጣጥሎ በመቐጠሉ ምክንያት የሞተዎች ንፁሃን ዜጎቻችን ሂወት በተለያዩ ጎደናዎች ወድቀው እንዲቀሩና በሺዎች ደግሞ እየተገረፉ ወደ እሱር ቤት እንዲታጎሩ እያድረገ መጥተዋል አሁንም እየቀጠለበት ይገኛል።
   ይህ ተቃዉሞ ዘላቂ መፍትሔ ሳያገኝ እየቀጠለና የዜጎች ሂወት እየበላ ይገኛል።ይህ እንዳለ ሆኖ በጎንደርና ባህርዳር ጀምሮ በመላው አማራ ክልል አንፃር የጨቛኙን ስርአት የተነሳው ህዝባዊ ተቃዉሞዎች ተከትሎ የክልሉ ተወላጆች በማሀል ጓዳና በጥይት እንዲረግፉ ችለዋል ብቻ ሳይሆን ስርአቱ በተከተለው ከፋፋይ ፖሊሲና አመለካከት የወለደው ምክንያት ለአመታት ተከባብረውና ተቀራርበው በክልሉ ሲኖሩ የቆዩ የትግራይ ክልል ተወላጆች የሆኑ ወገኖች በላያቸው ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንዲወርድባቸው በመቻሉ ተከትሎ ቁጥራቸው የማይናቁ በገዛ አገራቸው ሂወታቸው እንዲያልፍና አካላቸው እንዲጎድል ችለዋል በገዛ አገራቸውም እንደ ሁለተኛ ዜጋ ሆንው እንዲታዩና ተፈናቅለው ወደ ክልላቸው ሲገቡ ይታያሉ።  
     በተመሳሳይ በደቡብ ኢትዮጵያ በቢሄር ብሄረ ሰዎችና ህዝቦች  የሚገኙ የኮንሶ ብሄረ ሰብ ሐገ መንግስት በሚፍቅድላቸው መሰረት የአስተዳደር ጥያቅያቸው ለአመታት አቅርበው መልስ በማጣታቸው የተነሳ በሰላማዊ መንገድ ቅሬታቸው ስለ ገለፁ ብቻ ሞት ግርፋት እሱር እየደረሰባቸው እንዳለ የሚታወቅ ነው።
ይህና ሌላ ፖለቲካዊ ነዉጦች መፍትሔ ሳያገኙ ስርአቱ ተሃድሶ በሚል መዝሙር በሚያሰማበት ወቅት ነው በመስከረም 22 ቀን 2009 ዓ.ም በኦሮምያ ክልል  ቢሾፍቱ ከተማ የኢሬቻ ባህላዊ በአል በደመቀ መንገድ ለማክበር በሚልዮኖች የሚቆጠር ህዝብ በተገኘበት ጊዜ ኢህአዴግ እንደልማዱ በርከት ያለ የታጠቀ ሃይል በአሉ ወደ ሚከበርበት ቦታ በመላክ ራእድና ሽበራ መፍጠር በመቻሉ ህዝብ በኢሬቻ ባህላዊ በአላችን የሆነ ይሁን የመንግስት እጅ አስገቢነት አያስፈልግም ባህላዊ በአላችን በሰላም እንድናከብር ልቀቁልን በማለቱ ብቻ በሰላማዊ ህዝብ ላይ የጥይት እሩምታ እንዲዘንብና በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ወገኖቻችን በገደል እንዲፀድፉና ተፀቓቕጠው ሂወታቸው እንዲያጡ ምክንያት ሆነዋል።
 ይህ የወለደው የህዝብ ሃይለኛ ቁጣ ደግሞ ወደ ሁሉም አከባቢዎች ተስፋፍቶ እየቀጠለ በመኖሩ በየቀኑ የስርአቱ አንፃር ጥላቻ በቁጣ ወደ አደባባይ ወጥቶ መስዋእትነትና አካለ ጎዶሎነት እየከፈለ ይገኛል ስለዚህ ህዝባችን የሚያስፈልገው ዴሞክራሲና ህዝባዊ መንግስት በአጭር ጊዜ ለመረጋገጥ ሁሉም አይነት ትግላችን እናጠናክር እንላለን።


No comments:

Post a Comment