Thursday, October 6, 2016

የኲሓ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ንፅህናው ያልጠበቀ ውሃ ሰለሚጠቀሙ ለተለያዩ የውሃ ወለድ ተላላፊ ህመም እየተጠቁ መሆናቸው ተገለፀ።



   በመረጃው መሰረት የኲሓ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ ወገኖች በአከባቢያቸው ንፁህ የውሃ ቧንቧ እንዲቀርብላቸው በተከታታይ ለሚመለከተው አካሎች አቤቱታቸው ቢያቀርቡም እንኳ  ችግራቸውን አዳምጦ ዛላቂነት ያለው መፍትሄ የሚሰጥ አስተዳደር ባለማግኘታቸው  ምክንያት ማይ ሽብጢ ተብሎ ከሚጠራው ኣከባቢ የሚገኘውን ቆሻሻ ከሞላበት ኩሬ ስለሚጠቀሙ ለበሽታ መጋለጣቸውን በተለያዩ ሚድያዎች ካቀረቡት ሃሳብ ለመረዳት ተችለዋል።
የኲሓ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ጨምረው ሲገልፁ ይህ ችግር ከምናነሳው ብዙ   አመታቶች ኣልፈዋል ፤ በአከባቢያችን የውሃ ቧንቧ የሚባል ባለመኖሩና ለዚህም እንስሶችና ሰውም ኣብረን ወሃውን እየተጠቀምበት ነው ብለው መግለፃቸውና  የዂሓ ክፍለ ከተማ አስተዳዳሪ ብርሃነ ወለገብሪኤልና የመቀሌ ከተማ የወሃ አገልግሎት ሓላፊ ግደና አበበ በበኩሉ ችግሩ እናዉቀዋለን በግዝያዉነትም በቦጥ እናካፋፍላችውዋለን ቢልም ወገኖቹ ግን በቦጥ የሚከፋፈል ወሃም ሊዳረስ ባለመቻሉ አሁንም ንፅህናው ባልጠበቀ ወሃ ለመጠጥና ለተለያዩ አግልግሎቶች በመጠቀም ላይ መሆናቸው አስታዉቀዋል።
  በመጨረሻ የዂሓ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ያጋጠማቸዉን የንፁሕ ወሃ ችግር አማታትን ያስቖጠረ ቢሆንም የዛሬ ችግር ግን ግዜ ከ ማይሰጠው አጣዳፊ የተቕማጥ በሽታ እየተባባሰ በመሄድ ላይ ባለበት ጊዜ በቦታው ደግሞ የሚጠቀሙበት ቖሻሻ ወሃ በመጠጣት አንድ ሰው በመታመሙ ምክንያት ወደ ህዝብ እንዳይዛመት ከባድ ስጋት መፍጠሩን ከገለፀ በኋላ መንግስት አስቸዃይ መፍትሔ ሊያደርግላቸው ገልፀዋል።

No comments:

Post a Comment