Tuesday, March 6, 2018

የንፁኃንን ደም ደፍቶ መኖር ዘበት!!



በአምባገነኑ የወያኔ ኢህአዴግ ረገጣና ብልሹ አስተዳደር ያንገፈገፈው ህዝብ፣ ከብዙ ጊዜ ትግስትና መሽከም ተጨባጭ ለዉጥ ለማግኘት ባደረገዉ እንቅስቃሴ፣ ተገቢ ምላሽ እጥቶ በባሰ መልኩ ፍዳዉን እየበላ ይገኛል።
    በጨቋኙ የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት አነጣጥሮ የተነሳ የህዝብ እምቢተኝነት፣ ምንም መፍትሄ በሌለዉ ሂድ ሲሉት፣ ከዚህ ባለፈም ህገ-መንግስታዊ መብቱን ተጠቅሞ ቁጣዉን መግለጽ በሚፈልግበት የጸጥታ ሃይሎች በሱ ላይ ዘምተዉ ደሙን ሲያፈሱትና ህይወቱን ሲያሳጡት ብሎም፣ ወደ እስር ቤት ሲወረዉሩት እየታዩ ነዉ።  
   በመሆኑም ለዚህ የሃገራችን ህዝቦች ደመኛ የሆነ ስርዓት በቅጽበት ተወግዶ፣ ሌላ የተሻለ ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች የሚተማመኑበት፣ ባለምንም ዘረፋና ማጭበርበር ድምጻቸዉ በቅኑነትና ፍትሃዊ ምርጫ ተመስርቶ ህዝብና ሃገር የሚወክል የደለደለ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ለመትከል በመረባረብ ላይ ይገኛሉ።   
     የወያኔ ኢህአዴግ ቡድን ደግሞ በተነሳዉ የህዝብ እምቢታ ተናግቶ የተለያዩ ዉሳኔዎችና ፈጠራዎች ለማሴር ተገዷል። እንደምሳሌ ለመጥቀስ ያህል፣ በዚህ ቅርብ ግዜ ያለፈዉን ወር የኢህአዴግ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለ17 ቀናት ያካየደውን ግምገማ መሰረት አድርጎ፣ ራሱ ለፈጠረዉ አደጋ ይቅርታ ሊጠይቅለት እና ለመድረኩ ደግሞ እንደ መጨረሻ እድል አግኝቶ፣ ዘላቂ መፍትሄ አመጣለሁ ብሎ ቃል በገባበት ግዜ፣ ከወያኔ ኢህአደግ መፍትሄ አንጠብቅም የሚል የህዝቦች ቁጣን ለማየት በቅቷል። 
     በዚህ ደግሞ በከባድ ፍራቻና ጭንቀት ሊገባ መቻሉ ሳይወድ በግድ እስረኞችን በብዛት እንዲፈታና በምህረት ሲለቅ ታይቷል።ለዚህ ደግሞ መጀመሪያውንስ ኢትዮጵያዉያን ለአዉዳሚ የኢህአዴግ ስርአት በተለያዬ መንገድ በመቃወማቸዉ ነዉ የተለያዩ በስም ማጥፋት ክሶች ተወንጅለዉ፣ በቁጥጥር ስር እንዲገቡ የተደረገ እንጂ፣ መቼ ወንጀል ፈጸሙ የሚል ገብረ መልስ ተሰጥቶታል።    
   
     በዚህ ምክንያት ለሳምንታት ያህል አጀንዳ ሆኖ ከቆዬ በኋላ ሌላ ፈጠራ በማዘጋጀት፣ የጠቅላይ ሚኒስቴርነት ሹመት ማዉረድና በሌላ መቀየር የሚል መነጋገርያ አጀንዳ ተከፍቶ ብዙ ሰዉ የየራሱ አስተያየትና ሃሳብ ሲሰጠዉ ሰንብቷል።ቢሆንም ግን የኢህአዴግ ክፋትና ሴራ የአደባባይ ሚስጥር ስለ ሆነ፣ ባቀዳቸዉ አዲስ የሚመስሉ ክስተቶች ለህዝቡ ሊያረጋጋዉና እንደ ድሮዉም አታሎ ለማለፍ ቦታ አላገኘም። ለዚህ ደግሞ ያቺ የቀረችዉን የመጨረሻ የሽንፈት እርምጃዉ የግድ በሃይል መጨፍለቅ ስላለበት ዳግም የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ለማወጅ ተገዷል።       

     የተነሳዉ የህዝብ ጥያቄ ግን በተደነገገዉ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ሳይገደብ ለቀናቶች በደቡብ ህዝቦች ክልል፣ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች በከፊል አድማ ሲደረግ ታይቷል። ይህ ደግሞ ወያኔ ኢህአዴግ የሚያመጣዉ ለዉጥ የለም ጥያቄያችን የስርአት ለዉጥ ነዉ የሚል ነዉ መሰረቱ።
    ድምጻዊ ሃጎስ ገብረህይወት እንዳለዉ" መን ክነብር ምስ ደመኛታቱ አፍ ደገና ንዕጾ ክሳብ ዝሕተቱ" እንዳለዉ ነዉና እነዚህ የንጹህ ኢትዮጵያዊ ዜጋን ደም በአውራ ጎዳናዎች በድብቅና በግልጽ ሲያፈሱና ህይወት እንዲያሳልፉ የወጡ የክፋት ሴራ አመራሮች ባነሳነው ቃልና በከፈልነዉ መስዋእትነት ሁሉም አይነት እንቅፋትና ላግጣቸዉ አንዳንድ አመራሮች ማቀያየር ቀጥለዉበታል።      
     የሃገራችን ህዝቦች ግን የስልጣን ጥማትና ፉክክር ሳይሆን ይህ ሁሉ ስቃይ፣ እንግልት፣ ማሰር፣ ጉዳት፣ መስዋእትነትና ዉድመት በስርአቱ እንዲወርዳቸዉ እየተገደዱ ያሉ። ምንድነዉ ታድያ ከተባለ ለዚህ ሁሉ ስጋትና ዉድመት የፈጠረ ግለ አመራር ብቻ ሳይሆን ገዥዉ ፓርቲና እሱ የሚመራዉ መንግስት የሚከተለዉ የዉድመት ፖሊሲና ተግባራት ስለሆነ፣ ኢህአዴግ ስልጣኑ ለህዝብ እንዲያስረክብና በህግ ፊት ቀርቦ እንዲጠየቅ የሚል ነዉ።      
       ስለዚህ ፀረ ጨቋኙ የወያኔ ኢህአዴግ ስርዓት የጀመርነዉን ሁለንተናዊ የትግል አማራጮች በማጠናከር የሚፈለገውን የስርዓት ለዉጥ እስክናመጣ ትግላችን ቀጣይ ነዉ። የንጹሃንን ወገኖች ደም የደፋናየልጆቻችን  ህይወት የቀጠፈ አንባገነን ስርዓት፣ መፍትሄ ያመጣል ማለት ዘበት ሊባል ይገባል።  
   

No comments:

Post a Comment