Wednesday, July 17, 2013

በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ለአራት አመታት በርቀት ትምህርት መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ከ 500 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ቦንድ አልገዛችሁም በሚል ሰበብ በምረቃው ስነስርዓት እንዳይሳተፉ ተደረገ።



ተመራቂዎቹ አስፈላጊውን የትምህርት ክፍያ በመክፈል ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ሃምሌ 2005 ዓ/ም የሚሰጣቸውን ትምህርት አጠናቀው ዩኒቨርሲቲው በ2005 ዓ/ም ከሚያስመርቃቸው ተመራቂ ተማሪዎች ጋር በተለመደው ስነስርዓት መመረቅ ቢገባቸውን በዩኒቨርሲቲው ታግደዋል።   እገዳውን ተከትሎ ተማሪዎቹ እንደማንኛውም ተመራቂ በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች የምረቃ ስነስርዓት ለመሳተፍ ጥያቄ ቢያቀርቡም ቦንድ ስላልገዛችሁ በምረቃው ስነስርዓት መሳተፍ አይፈቀድላችሁም በማለት የምረቃው ቀን ከአለፈ ብሁዋላ ተማሪዎቹ በየግላቸው ወደ ዩኒቨሲቲው ሬጅስተራር ጽ/ቤት ድረስ በመሄድ ዲግሪያቸውን እንደ ተራ ነገር መውሰዳቸውን ቷውቋል።
ይህ በእንዲህ እያለ በአማራ ክልል በባህርዳር ከተማ በጥብቅና ሞያ የተሰማሩ ጠበቃዎች ከሚያገኙት ገቢ የተወሰነ ገንዘብ እንዲያካፍሉት የክልሉ የፍትህ ቢሮ ሃላፊ ጠይቃቸው ፈቃደኛ ያልሆኑ ጠበቃዎች ሰበብ በመፍጠር ከስራቸው እንዲታገዱ ተደርጓል።
እገዳው የተጣለባቸው በጥብቅና ሞያ የተሰማሩ ባለሞያዎች እገዳው አግባብነት የሌለው በመሆኑ እንዲነሳላቸው ወደ እሚመለከተው የፌደራል አካል በመሄድ ክስ ቢያቀርቡም በአከባቢያችሁ ካሉት ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለስልጣናት ጋር ተነጋግራችሁ ፍቱት እኛ የምንሰጣችሁ ምላሽ የለም በማለት እንደመለሳቸው ለማወቅ ተችሏል።