ቦታው ለስኳር ልማት ፕሮጀችት ይፈለጋል በሚል ምክንያት ከቀያቸው በጸጥታ ሃይሎች ተገደው እንዲነሱ የተደረጉ
ሰዎች ቁጥር 600 የሚደርስ ሆኖ በአሁኑ ጊዜ ባዶ ሜዳ ላይ ወድቀው
ዝናብና ብርድ እየተፈራረቀባቸው በከባድ ችግር ላይ ይገኛሉ። ተፈናቃዮቹ መጀመሪያ ተለዋጭ መሬትና የንብረታችሁ ግምት ካሳ ይሰጣችሃል
የሚል ቃል የተገባላቸው ቢሆንም እሳካሁን ድረስ ስላልተተገበረ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ለሚመለከተው አካል ጥያቄ ባቀረቡበት ጊዜ ቦንድ
ስላልገዛችሁ በመንግስት የሚሰጣችሁ ካሳ የለም የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ቷውቋል።
ተፈናቃዮቹ ጥያቄያቸውን ለወረዳና ዞን አቅርበው ምላሽ ስላላገኙ ከመካከላቸው አቶ ሕሉፍ አስገዶም ፤ አቶ
አስማማውና ወ/ሮ አሰፋች ግደይ የተባሉ ሦስት ሰዎችን በመመረጥ ለክልሉ መስተዳድር ክስ ቢያቀርቡም የምናውቀው ነገር የለም የሚል
ተመሳሳይ ምላሽ እንደተሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል።