በደረሰን ዘገባ መሰረት የአማራ ክልል የጸጥታ ሃላፊ የሆኑት አቶ አድማሱ ይልማ ለስራ ተብሎ የተሰጠውን
የተለያየ ዓይነትና ብዛት ያላቸው ክላሽና ሽጉጦች ሃላፊነቱን ወደ ጎን በመተው ስልጣኑን አለአግባብ በመጠቀም የግል ፍላጎቱን በማስቀደም
በህገ ውጥ መንገድ ሃብት ለማካበት ከነጋዴዎች ጋር በመመሳጠር በርካታ የጦር መሳሪያዎች የሸጠ ሲሆን ህገወጥ ነጋዴዎቹ በህዝብ ትብብር
በቁጥጥር ስር በመዋላቸው ባለስልጣኑ ሊጋለጡ ችሏል።
ከክልሉ የጸጥታ ሃላፊ የጦር መሳሪያ የገዙ አቶ ሰለሞን ባህታና አቶ ይፍጠር የተባሉ ነጋዴዎች ሲሆኑ ግለሰቦቹ
በቁጥጥር ስር ከዋሉ ብሁዋላ አንዱን ክላሽ በ 25 ሽህ ብር እንዲሁም አንዱን ሽጉጥ በ 15 ሽህ ብር ሂሳብ በርካታ የጦር መሳሪያ
ህጋዊ አስመስሎ እንደሸጠላቸው በመግልጽ የገዛነው መሳሪያ ህገ ወጥ ከሆነ እኛ ሳንሆን የክልሉ የጸጥታ ሃላፊ ነው በቁጥጥር ስር
ውሎ መጀመሪያ መጠየቅ ያለበት ሲሉ መናገራቸውን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።
ነጋዴዎቹ ከገዛቸው የጦር መሳሪያዎች ጋር በእግዚቢት ተይዘው በክልሉ ፖሊስ ስር የሚገኙ ሲሆን ባለስልጣኑ
ግን በህግ ቁጥጥር ስር መዋል ይቅርና ስለተፈጸመው ወንጀልም ቢሆን ወደ ህግ ቀርቦ እንዲጠየቅና ቃሉ እንዲሰጥ አልተደረገም ፥ ሁኔታው
ስርዓቱ ምን ያህል በሙስና መጨማለቁን የሚያመላክት መሆኑን በሰፊው ይነገራል።