Wednesday, July 17, 2013

የኮሙኒኬሽን ሰራተኞች በሙስና የተጨማለቁ ባለስልጣናትን ወደ ሌላ ክፍል ተዛውረው እንዲሰሩ ማድረግ አግባብነት የለውም በማለት ተቋውማቸውን ገለጹ።



ሃምሌ 5,2005 ዓ/ም በኮሙኒኬሽኑ ጽ/ቤት የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ዋና ዓላማው የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች የሆኑ አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ኩማ ደመቅሳ የህዝቡን ሃብት ዘርፈው ለግል ጥቅማቸው በማዋል በሙስና በመዘፈቃቸው በህግ እንዲጠየቁ ከህዝብ ጥያቄ እየቀረበ ባለበት በአሁኑ ወቅት ከነበሩበት ጽ/ቤት ተዛውረው በሌላ ቦታ እንዲሰሩ መደረጉ ህጋዊነት የለውም በማለት የተካሄደ መሆኑን ቷውቋል።
ሰላማዊ ሰልፎኞቹ በጸረ-ሙስና ኮሚሽን የሚደረግ ቁጥጥር አድልዎንና ጥቅማጥቅምን መሰረት ያደረገ መሆኑን በመግለጽ በኢህአዴግ አመራሮች በቢልዮን የሚቆጠር ገንዘብ እየባከነ እያለ ሃይ የሚል ጠፍቶ በዝምታ ሲታለፍ እንዳልነበረ ሁሉ አሁን ደርሶ እነ አቶ መላኩ ፋንታን በቁጥጥር ስር ማዋል ግለሰቦችን በእስር ቤት ለማጎር ስለተፈለገ እንጂ ሙስናን ለመዋጋት ተፈልጎ አይደለም በማለት ያስረዳሉ።
      ሰላማዊ ሰልፍን ያስተባበሩ የአ/አበባ ከተማ ከንቲባ ጸሃፊ የነበሩ ወ/ሮ ምህረት ሃይሉና የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የጸጥታ ሃላፊ የሆኑት አቶ ከበደ ጫቅሌ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።