በአማራ ክልል፤ በመተማ ወረዳ በተደጋጋሚ በሚታየው የዝርፊያና የግድያ ተግባር የተነሳ የአከባቢው ኗሪ ህዝብ
ለህይወቱም ሆነ ለንብረቱ ዋስትና የሚሰጠው አካል አጥቶ በችግር ላይ ይገኛል። በተለይም በአሁኑ ጊዜ በከተማዋ እየተበራከተ የመጣው
በሌቦች የሚፈጸም ዝርፊያና ግድያ እንዳይበቃ የከተማዋን ጸጥታ እንዲያስከብሩ በመንግስት በተላኩ የፖሊስ አባላት የሚፈጸም ተመሳሳይ
ተግባር ተጨምሮበት ሌባና ፖሊስ መለየት ስላልተቻለ የአከባቢው ህብረተሰብ አቤት የሚልበት ቦታ አጥቶ በስጋት ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ
ተችሏል።
እንዲህ
ባለው አነዋሪ ተግባር በከተማዋ ጸጥታን እንዲያስከብሩ በተሰማሩ የፖሊስ አባላት የማይጸብሪ ከተማ ተወላጅ የሆነው አቶ አሳምነው
ግርማ የተባለ ነጋዴን ጨለማን ተገን በማድረግ ገንዘብ እንዲሰጣቸው ጠይቀውት ነገር ግን ነጋዴው የተጠየቀውን ገንዘብ ለመስጠት ፈቃደኛ
ስላልሆነ ሁለት የፖሊስ አባላት እንግዲያውስ በወንጀል ትፈለጋለህ በማለት እየቀጠቀጡ ከወሰዱት ብሁዋላ በበነገታው ጠዋት መንገድ
ላይ ሞቶ ወድቆ ተገኝቷል፣ የከተማዋ ኗሪዎች ግለሰቡን የገደሉት የፖሊስ አባላት መሆናቸውን በመግለጽ ድርጊቱን አውገዘዋል።