Monday, July 22, 2013

በሽረ-እንዳስልሰ ከተማ የመስተዳድር አካላት እየተፈጸመ ያለው የሙስና ተግባርን ለመሸፈንና በየበታች ሰራተኞች እንደተፈጸመ ለማስመሰል የጀመሩትን የበታች ሰራተኞችን የማሰር ተግባር የከተማዋ ኗሪ ህዝብ ተቃወመ።



በከተማዋ በሚገኙ ቀበሌዎች የኢህአዴግ ስርዓት ታማኞች የሆኑ ባለስልጣናት የግል ጥቅማቸውን ስለሚያስቀድሙ በምስና የተዘፈቁ ናቸው፣ ማንኛውም የከተማዋ ኗሪ የመታወቅያ ካርድን ሳይቀር እንዲሰጠው በሚጠይቅበት ጊዜ በዛሬ ነገ እያመላለሱ ጉቦ ለሚስጥ ሰው ግን በቀላሉ እንዲፈጸምለት ያደርጋሉ፣ በዚህ ኣካሄድ ባለስልጣኖቹ ማንነታቸው ለማይታወቁ ሰዎች ሳይቀር የመታወቂያ ካርድን ስለሸጡና ሚስጥሩም በምጋለጡ እራሳቸውን ለማዳን ሲሉ የበታች ሰራተኞች የፈጸሙት በምስመሰል በስራቸው የሚገኙ ሰራተኞችን ተጠያቂ እንዲሆኑ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
በቀቤሌ የመስተዳድር አካላት የተፈጸመው የመታወቅያ ካርድን የመሸጥ ተግባር በሁሉም ቀበሌዎች የሚታይ ሆኖ በተለይም በ 01 ና 05 ቀበሌ በሰፊው ሲሰራበት የቆየ ነው፣ በአሁኑ ጊዜ ሁኔታው በከተማዋ ኗሪ ህዝብ ስለተደረሰበት የ01 ቀበሌ አስስተዳደር በስሩ የምትገኝ የቀበሌው የመዝገብ ቤት ሰራተኛ ወ/ሮ ፋና ፍስሀን እንደዚሁም የ 05 ቀበሌ አስተዳደሪ የቀበሌው የመዝገብ ቤት ሰራተኛ የሆነችውን ወ/ሮ አጸደ ሃይሉን ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ሰብብ በውሸት ክስ እንዲሰሩ ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል።
        ሂደቱን በጥንቃቄ ሲከታተል የነበረው የከተማዋ ኗሪ ህዝብ ወንጀሉ የተፈጸመው በቀበሌ የመስተዳድር አካላት እንጂ በመዘብ ቤት የበታች ሰራተኞች አይደለም በማለት ሰራተኞች በነጻ እንዲለቀቁ በምትኩ ባለስልጣናቱ ወደ ፍትህ እንዲቀርቡ በመጠየቅ ተቃውመውን መግለጹን ከከተማዋ የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።