በከተማዋ የተለያዩ መጋዝኖችና የንግድ ድርጅቶች በተደጋጋሚ ይዘረፋሉ። ዘረፋው የሚፈጸመው በሌሊት ሲሆን
ተበዳዮቹ ሁኔታውን እንዲጣራላቸው ለፖሊስ ቢያመለክቱም ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ሃላፊነት ወስዶ የሚያጣራ አካል ይለም፣ ይልቁንም የከተማዋ
የፖሊስ ጽ/ቤት ህብረተሰቡን ማገልገል ሲገባው ከሌቦች ጋር ሲተባበር ይታያል።
በዚህ የፖሊስ አባላትና ሌቦች በመተባበር በከተማዋ ኗሪዎች ላይ እየተፈጸመ ባለው የዝርፊያ ተግባር ንብረትነቱ
የአቶ ሃፍቶም ካሕሳይ የተባሉ በከተማዋ የኮካ ኮላ ማከፋፈያ ያላቸው ነጋዴ የሆነ አንድ መጋዝን ሰኔ 14,2005 ዓ/ም በመስበር
ከ 200ሽህ በላይ ጥሬ ገንዘብ ፤ ቴለቪዥን ፤ሞባይልና ሌሎች ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን መዘረፋቸውን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
የአካባቢው ኗሪዎች መንገሻ የተባለ አንድ የፖሊስ አባል ከዘራፊዎቹ ጋር እንደነበረና ፖሊስና ሌቦች ተባብረው
ዘረፋውን እንደፈጸሙት በመግለጽ ለሚመለከተው አካል ዝርዝር ማስረጃ ቢያቀርቡም እስካሁን ድረስ የተወሰደ ምንም ዓይነት እርምጃ የለም።