በደረሰን ዘገባ መሰረት ንብረትነቱ የአማራ ክልል የገጠር ልማት ቢሮ ሆኖ በክልሉ ለሚካሄድ የአፈርና ውሃ
ጥበቃ ስራ ተብሎ በመንግስት የተገዛ በአስር ሽዎች የሚቆጠር አካፋና ዶማ ሲሆን ንብረቱ በህጋዊ መንገድ ለስራ እንደተላከ በማስመሰል
በትግራይ ክልል ውስጥ እንዲሸጥ የተጫነ እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል።
ንብረቱን
የጫነች አይስዙ የሰሌዳ ቁጥራ 00139 ሲሆን 20 ሽህ አካፋና 15 ሽህ ድማ ጭና ነበር። ደባርቅ ከተማ በሚገኘው የፍተሻ ኬላ
ስትደርስ በኬላው ሰራተኞች ብትያዝም የፍተሻ ኬላው ሃላፊ ሃምሳ አለቃ ጉግሳ ረዳ ንብረቱን እንዲያልፍ ከፈለጋችሁ ጉቦ መክፈል አለባችሁ
በማለት በሌላ ሦስተኛ ሰው በኩል በአማራ ክልል እርሻና ገጠር ልማት ቢሮ ንብረቱን እዲሽጡ ለተላኩት ተወካዮች በጠየቀው መሰረት
3 ሽህ ብር ጉቦ ከሰጡት ብሁዋላ መኪናዋ ከጫነችው ንብረት ጋር እንድታልፍ መፍቀዱን ለማወቅ ተችሏል።