Monday, July 22, 2013

ከሽረ-እንዳስላሰ ከተማ ወደ ጎንደር በሚወስደው የመኪና መንገድ በሚገኘው የተከዘ ወንዝ ድልድይ ላይ ለጥበቃ የተሰማሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተገደሉ።



የኢህአዴግ መንግስት ፤ በትግራይ ክልል በአስገደ ጽምብላና በጸለምቲ ወረዳ መካከል በሚገኘው የተከዘ ወንዝ ድልድይ የአከባቢውን ጸጥታ እንዲጠብቁ ካሰማራቸው የፌደራል ፖሊስ አባልት ውስጥ ሁለት አባላት ሀምሌ 5,2013 ዓ/ም ሌሊት ተገድለው ማደራቸውንና የገዳዮችን ማንነት እስካሁን ድረስ እንዳልታወቀ ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
በሚያገኙት ዝቅተኛ ደምዎዝ ተታለው የኢህአዴግን ስርዓት በማገልገል በተከዘ በረሃ በጥበቃ ስራ ተሰማርተው የሚገኙ የፌደራል ፖሊስ አባላት ለጊዚያዊ ጥቅም ካልሆነ ስርዓቱን ለማገልገል እምነት እንደሌላቸው ዘገባው ጠቅሶ በተለያዩ አጋጣሚዎች አደጋ ለሚደርስባቸው ዋስትና እንደማይሰጥና ለቤተሰቦቻቸውንም ምንም ዓይነት ድጋፍ እንደማይደረግ በዓይናቸው ስለሚያዩ በየቀኑ የሚጠፉ የፌደራል ፖሊስ አባላት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመሄድ ላይ መሆኑን የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።