Thursday, October 10, 2013

የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ት.ህ.ዴ.ንና የኢትዮጵያ ህዝቦች ለፍትህና እኩልነት ግንባር(ኢ.ህ.ፍ.እ.ግ) ከመስከረም 18,2006 ዓ/ም ጀምሮ በውህደት ለመስራት መስማማታቸውን ባወጡት የጋራ መግለጫ ገለጹ፣




የጋራ መግለጫው የኢትዮጵያ ህዝብ ከሚደርስበት ጭቅናና ስቃይ እራሱን ነጻ ለማውጣትና መብቱን ለማስከበር ለዓያሌ አመታት ያካሄደው እልህ አስጨራሽ ትግል በህዝብ ስም በሚነግዱና በሃገሪቱ እየተፈራረቁ ወደ ስልጣን በሚመጡ አምባገነኖች መብቱ እየተረገጠ ምኞቱ ሳይሰምርለት አሁንም በአስከፊ ሁኔታ እንደሚገ ጠቅሶ በተለይም የህዝብን ጥያቄን መነሻ በማድረግ የተነሳው የኢህአዴግ ስርዓት፤ የአገሪቱ ጭቁን ህዝቦች ነጻነታቸውንና መብታቸውን ለማስጠበቅ ያካሄዱት ወደር የለሽ መራራ የትጥቅ ትግል፤ የተከፈለው መስዋእትነት፤ የተነሳለት ህዝባዊ ዓላማና የሰማእታትን አደራ በመካድ ከደርግ ስርዓት በከፋ መልኩ ህዝቡን በማፈን፤ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶችን በመርገጥና ሁሉንም የሰላማዊ ዴሞክራሲያዊ ትግል አማራጮችን በመዝጋት እራሱን አውራ ፓርቲ ብሎ በመሰየም በማን አለብኝነት አምባገነናዊ አገዛዙን አጠናክሮ ቀጥሎበታል ሲል ገልጻል፣
አምባገነኑን የኢህአዴግ ስርዓትን በመቃወም በርካት የፖለቲካ ድርጅቶች በየአቅጣጫው በተናጠል የትጥቅ ትግልን ጨምሮ ሰላማዊ ፖለቲካዊ ትግል ማካሄዳቸው የሚደገፍ ቢሆንም ውህደት ፈጥረው መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው እንደ አገር የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት እንዳልተቻለ በማመልከት በዚህ ረገድ ትህዴንና ኢ.ህ.ፍ.እ.ግ የህዝቡን አንገብጋቢ ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ የአገሪቱን ሁኔታ በጥልቀት በመገምገምና በውህደት የመስራት አስፈላጊነት በመረዳት ከአመታት በፊት የጀመሩትን ተባብሮ የመስራት ልምድ በማጠናከር ከመስከረም 18,2006 ዓ/ም ጀምሮ በውህደት ለመንቀሳቀስ መስማማታቸውን ባወጡት የጋራ መግለጫ ገጸዋል፣
መግለጫው ሁሉንም የኢህአዴግን ስርዓት በመቃወም የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች በውህደት መስራት ወቅታዊና አስፈላጊ መሆኑን ተገንዝበው የኛን ፈለግ እንዲከተሉ ሲል ጥሪ አቅርባል፣