Thursday, October 10, 2013

የኢህአዴግን ብልሹ አሰራር በመቃወም በመተማ በኩል ወደ ሱዳን ከተሻገሩት ወጣቶች መካከል አራት አራቱ ሲገደሉ በስዱስቱ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፣



ከወሎና ከጎንደር የተነሱ ቁጥራቸው ከ 65 በላይ የሚሆኑ ሴቶች የሚገኙባቸው ወጣቶች በመተማ ከተማ በመሰባሰብና አንዲት አውቶብስ በመኮናተር ማልያ ለብሰው እስፖርተኞች መስለው የኢትዮጵያን ባንዲራ እያውለበለቡ ኬላ ጠባቂዎችን በማታለል መስከረም 22,2006 ዓ/ም ድምበር ተሻግረው ሱዳን ‘ዳብራል’ በተባለ ቦታ ከደረሱ ብሁዋላ የኢህአዴግ የፀጥታ ሃይሎች በአከባቢው ደርሰው ለመያዝ ባደረጉት ሙከራ አብዛኛዎቹ በየአቅጣጫው ሲበታተኑ አራቱ በተተኮሰባቸው ጥይት ወዲያውኑ ሲሞቱ ሌሎች ስድስት ላይ ከባድ ጉዳት ደርሳል፣
በጸጥታ ሃይሎች በተተኮሰባቸው ጥይት ከተገደሉት ዜጎች መካከል ተመስገን አድማሱ ፤ ሪሒማ ይማም ፤ ህሊና አበበና ክብሩ ክንፈ ሲሆኑ በወቅቱ አመራር ሲሰጡ የነበሩ የኢህአዴግ የጸጥታ አመራሮች ደግሞ ምክትል ኢንስፔክተር ተስፋየ ላቀውና ምክትል ኢንስፔክተር ሰለሞን አረጋዊ መሆናቸው ቷውቋል፣