ትህዴን የትጥቅ ትግል በማካሄድ ላይ ከሚገኘው ጉንበት-7 ጋር ተባብሮ ለመስራት መግባባት ላይ ከመድረሱም
በላይ በተግባር በተለያየ መልኩ ሲተጋገዙ የቆዩ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተለያዩ ሃገራት የሚገኙ የትህዴን አባላት የጉንበት-7
አመራር ከአባላቱ ጋር በተለያዩ ሃገራት እያካሄደው ባለ ስብሰባ በመገኘት አንድነታችንን አጠናክረን እጅ ለእጅ ተያይዘን እንሰራለን
ሲሉ ለጉንበት-7 ያላቸውን ድጋፍ መግለጻቸውን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
በስብሰባው የተገኙ የትህዴን ተወካዮች አያይዘው እኛ በዚሁ ስብሰባ ስንገኝ ለይምሰል ሳይሆን የህዝብን ድምጽ
በአፈሙዝ ረግጦ ስልጣን የተቆናጠጠውን ከፋፋዩን የኢህአዴግ ስርዓትን በሚገባው ቋንቋ በትጥቅ ትግል ከስሩ መንግሎ ለመጣል ገና ከመነሻው
ትህዴን አምኖበት የተነሳለት በመሆኑ የድርጅቱን ዓላማ እግቡ ለማድረስ የሁለቱም ድርጅቶች አባላትና ደጋፊዎች የኢህአዴግ ስርዓት
መለያ ከሆነው በዘር የመከፋፈል አባዜ በመውጣት በሙሉ ልብ ድርጊቱን በማውገዝ ከሃገር ውስጥ ይሁን ከሃገር ውጭ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች
ከመቸውም ጊዜ በላይ ግንኝነታችንን አጠናክረን ተባብረን መስራት ይጠበቅብናል በማለት ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፣
የጉንበት-7 አመራርና አባላት በቡኩላቸው የትጥቅ ትግል በማድረግ ላይ ካሉት ተቃዋሚ ድርጅቶች በመሳሪያ
፤ በሰው ሃይልና በዓላማ ሲታይ ትህዴን ጠንካራ መሆኑን በመግለጽ እንዲህ ካለው አስተማማኝ ድርጅት ጋር ተባብሮ ለመስራት ከመግባባት
አልፈን አብረን እየሰራን ነው፣ ይህ መልካም ጅምር አጠናክረን እንቀጥልበትአለን ሲሉ መግለጻቸውን የደረሰን ዘገባ ያስረዳል፣