በደረሰን ዘገባ መሰረት በሑመራ ከተማ ከ 18-22 የእድሜ ክልል የሚገኙ 10ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ተማሪዎች
ውትድርና እንዲመለመሉ ቅስቀሳ እየተደረገ ሲሆን ፥ የስርዓቱ ካድሬዎች ውትድርናን የተመለመለ የትምህርት ደረጃው እየታየ በኮምፒዩተር
፤ በመካኒክና ሌሎች ሞያ እንዲሰለጥን ይደረጋል የሚል የማይተገበር ቃል እየገቡ ወጣቱን ለማታለል ቢሞክሩም ወጣቶቹና ቤተሰቦቻቸው
ግን ቅስቀሳ ለማዘናጋት የሚደረግ የተለመደ ነገር መሆኑን በመገንዘብ ውድቅ ማድረጋቸውን ለመረዳት ተችሏል፣
ከዚህ ቀደም ባቀረብነው የዜና ዘገባ በመከላከያ ሰራዊት የብሄረ ትግራይ ተወላጆች ቁጥር በተለያየ ምክንያት
እየተመናመነ ስለመጣ በልዩ የምልመላ አሰራር ከክልሉ ወጣቶችን ለመመልመል እንቅስቃሴ መጀመሩን መዘገባባችን የሚታወስ ነው፣