መስከረም 19/2006 ዓ/ም በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ የተደረገው ስብሰባ በዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የኢኮኖሚ
ጉዳይ ሃላፊ አቶ ኢልሴፍ ታደሰ የተመራ ሲሆን በዞኑ የሚገኙ ሁሉም አስተማሪዎች በስብሰባው ተገኝተዋል፣ የስብሰባው አጀንዳም ለመለስ
ፋውንዴሽን ገንዘብ ስለ ማዋጣት የተመለከተ ሆኖ አስተማሪዎቹን በማሳመን በመለስ ፋውንዴሽን ስም ገንዘብ ማሰባሰብ በሚል ዓላማ የተደረገ
ነው፣ በስብሰባው በኑሮ ውድነትና በመንግስት መዋጮ ብዛት በሚከፈለን ደምዎዝ ህይወታችንን መምራት በማንችልበት ሁኔታ ገንዘብ ለማዋጣት
ፈቃደኛ አይደለንም ሲሉ አስተማሪዎቹ ተቃውማቸውን ገልጸዋል፣
መንግስት በሚጠይቀው ማለቅያ የሌለው የመዋጮ ዓይነትና ብዛት አስተማሪው ለፍቶ በወር የሚያገኘውን ደምዎዝ
በመንግስት መዋጮ እየተነጠቀ በከባድ ችግር ወድቆ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅት ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲዋጣ መንግስት መጠየቁ
እጅግ የሚያሳዝን ነው፣ መንግስት ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እዳስመዘገበ እየገለጸ ስለሆነ በራሱ ወጪ ሊሰራው ይገባል በማለት ከ
3 ሽህ በላይ የሚገመቱ አስተማሪዎች ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል፣