Tuesday, October 8, 2013

የትግራይና የኦሮሚያ ክልሎች ሙስና በከፋ መልኩ የሚታይባቸው ክልሎች መሆናቸውን በያዝነው ሳምንት የተካሄደ ገምጋሚ ጥናት አረጋገጠ፣



ዩ.ኤስ.አር.ዩ የተባለ በአፍሪካ ደረጃ የሚንቀሳቀስ መንግስታዊ ያልሆነ ጸረ-ሙስና ተቋም መስከረም 21,2006 ዓ/ም በመቐለ ከተማ ባካሄደው በሃገር ተቆርቋሪ በሆኑ ሙሁራንና ባለሞያዎች ያሳተፈ ውይይት ኢትዮጵያ ካላት ኢኮኖሚያዊ አቅም አንጻር ሲታይ ከአፍሪካ ሙስናና ብልሹ አሰራር በከፋ መልኩ የነገሰባት አገር ስትሆን በክልሎች አንጻር ሲታይ ደግሞ በትግራይና በኦሮሚያ ክልሎች ሙስናና ብልሹ አሰራር ስር የሰደደ መሆኑን ግልጽ አድርጓል፣
በመጨረሻም ዩ.ኤስ.አር.ዩ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው አገዛዝ ከላይ እስከ ታች በሙስና በመተሳሰር የሃገሪቱን ሃብት በመዝረፍ ላይ መሆኑን ጠቅሶ ከአሁን ብሁዋላ ከድርጅቱ ጋር ግንኝነት ያላቸው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ሁሉ ለአገሪቱ እርዳታ እንዳይሰጡ እንደሚሰራ አስታውቋል፣