በትግራይ ደቡባዊ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የሚኖሩ ገብሬዎች ለመስኖ እርሻ የሚውል ማዳበሪያ እንዲገዙ በኢህአዴግ
ካድሬዎች ከመስከረም 20,2006 ዓ/ም ጀምሮ ሰፊ ቅስቀሳ እየተደረገ ቢሆንም በመንግስት እየቀረበ ያለ ማዳበሪያ ዋጋው እጅግ ውድ
በመሆኑ ከምናመርተው ምርት ጋር የሚጣጣም አይደለም፣ ዓመት ሙሉ ደክመን የምናተርፈው ነገር የለም በማለት ገበሬዎቹ ተቃውማቸውን
ገልጸዋል፣
ገበሬዎቹ ፤ በስርዓቱ ካድሪዎች በተለይም አበበ ተስፋይ በተባለ የእርሻ ምርምር ወኪል መንግስት በሚያቀርብላችሁ
ማዳበሪያ ተጠቅማችሁ በሄክታር እክሰ 80 ኩንታል ምርት ማግኘት ትችላላችሁ የሚል አባባል በመቃወም የህዝቡን ስሜት ሲያስተጋቡ ከነበሩ
ኗሪዎች መካከል አቶ ሃፍቲ መንገሻ ፤ ወ/ሮ አጸደ ይኹኖ ፤ አቶ ገብረመድህን ይርሳውና ሌሎች ይገኙበታል ፣ መንግስት ለራሱ ካልሆነ
ለገበሬው አስቦ የሚያደርገው ምንም ነገር የለም በማለት በመንግስት ካድሪዎች ሲደረግ የነበረውን ጉትጎታ ውድቅ አድርገውታል፣