Tuesday, October 8, 2013

መንግስት በሸራሮ ከተማ የሚገኙ ነጋዴዎችን መክፈል ከሚገባቸው በላይ ከፍተኛ ግብር እንዲከፍሉ እያስገደደ ነው፣



በከተማዋ የሚገኙ ነጋዴዎች ከሚያገኙት ገቢ ጋር የማይመጣጠን ከፍተኛ ግብር በተደጋጋሚ እንዲከፍሉ ስለሚደረግ ለኪሳራ ተዳርገው የንግድ ድርጅታቸውን ለመዝጋት ተገደዋል፣ መንግስት በጫነባቸው ከፍተኛ ግብር ምክንያት የንግድ ድርጅታቸውን ከዘጉ የተለያዩ ነጋዴዎች መካከል።-
1-አቶ አስማረ አረጋይ በከተማዋ የህንጻ መሳሪያ መሸጫ ድርጅት የነበራቸው
2-አቶ ሰለሞን(ነባር ታጋይ) የሸቀጣ ሸቀጥ መሸጫ ሱቅ የነበራቸው
3-አቶ ቀበር በከተማዋ የሸቀጣ ሸቀጥ መሸጫ ሱቅ የነበራቸው የሚገኙባቸው ሲሆን ነጋዴዎቹ ድርጅቶቻቸው ስለተዘጉ ቤተሰቦቻቸውን ማስተዳደር በማይችሉበት ሁኔታ ይገኛሉ፣ በተለይም አቶ አስማረ አረጋይ የጭነት መኪና ገዝተው ለመንቀሳቀስ ሞክረው በከተማዋ መስተዳድር ፈቃድ መከልከላቸውን የደረሰን ዘገባ ያስረዳል፣