በሰለኽለኻ ከተማ በአንድነትና ቅንጅት የተካሄደው የፖለቲካ ቅስቀሳ ስኬታማ የነብረ ሲሆን የከተማዋ ኗሪዎች
የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ወደ ከተማዋ መጥተው ከህዙ ጋር በመገናኘት ዓላማቸውን በማስተዋወቃቸው ከፍተና ደስታ እንደሰጣቸው ገልጸው ከፖለቲካ
ቅስቀሳ ብሁዋላ በከተማዋ በሚገኘው የካቲት ሆቴል ቅስቀሳ ሲያደርጉ ለነበሩት የአንድነትና ቅንጅት ፓርቲ አመራሮችን የእንኳን ደህና
መጣችሁ መስተንግዶ እንዳደረጉላቸው ቷውቋል፣
በኢህአዴግ ስርዓት እግጅ የተማረሩት የከተማዋ ኗሪዎች አጋጣሚውን በመጠቀም ጸረ-ዴሞክራሲውን ስርዓት በመቃወም
ሃሳባቸውን የገለጹ ሲሆን ወደፊት ከተቃዋሚዎች ጎን በመሰልፍ ትግላቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉበት አረጋግጠዋል፣
የከተማዋ
ኗሪዎች ፋሽሽቱን የደርግ ስርዓት ለመደምሰስ በተደረገው መራራ ትግል ከፍተኛ የትግራይ ህዝብ ድጋፍ የነብረው ህወሓት-ኢህኢደግ ስልጣን
ከተቆናጠጠ ብሁዋላ ለጥቂቶች እንጂ ለህዝቡ የፈየደው ነገር ስለሌለ ጸረ-ዴሞክራሲውን ስርዓት ገርስሰን ህዝባዊ መንግስት ለመትከል
ዝግጁ ነን ሲሉ አቃማቸውን ገልጸዋል፣