Sunday, October 6, 2013

በግምባታ ላይ ያለው የወልቃይት የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀችት ሃላፊዎች ለፕሮጀችቱ ስራ የሚላከውን ንብረት በመሸጥ ለግል ጥቅማቸው አዋሉት፣



በያዝነው ሳምንት ለወልቃይት ስኳር ፕሮጀችት ተብሎ የተላከውን ስሚንቶ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ኮድ 3 የሰሌዳ ቁጥሩ 00888 የሆነ አንድ ከባድ ተሽከርካሪ በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ በአቶ ረዘነ መጋዝን ያራገፈ ሲሆን ፥ በኮድ 3 የሰሌዳ ቁጥሩ 22494 የሆነ አንድ ተሽከርካሪ ደግሞ በተሳቢው ጭኖት የነበረ ነዳጅ ፈሰሰብን በሚል ሰበብ ሸጠው ለግል ጥቅማቸው አውለውታል፣
የፋብሪካው ግምባታ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ እንዳለ በማስመሰል በስርዓቱ ሚድያ ነጋ ጠባ ቢነገርም ለፋብሪካው ግምባታ ተብሎ በህዝብ ገንዘብ ተገዝቶ የሚላከው ንብረት ግን በትክክለኛው ቦታ ሳይደርስ አየር ባየር እየተሸጠ በግለሶቦች ኪስ ስለሚገባ ስራው በእጅጉ መጓተቱን የደረሰን ዘገባ ያመልከታል፣