በሙስና ከተጨማለቁት የስርዓቱ ባለስልጣናት አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ላቅ
አያሌው ለከተማዋ መሰረተ ልማት ተብሎ ከተመደበው በጀት በስሩ ከሚገኘው የፋይናንስ ሃላፊ በመመሳጠር ከግማሽ ሚልዮን ብር በላይ
በተለያዩ ምክንያት ወጪ በማድረግ ለግል ጥቅማቸው እንዳዋሉት ቷውቋል፣
ከንቲባው በስሩ በየደረጃው በተለያዩ ሃላፊነት ካሉ ሃላፊዎች ጋር በመተሳሰር ሲፈጽመው የነበረ የሙስና ተግባር
የከተማዋ ኗሪ ህዝብ ተከታትሎ ቢያጋልጠውም ሃገሪቱን እየገዛ ያለው ስርዓት በሙስና የተጨማለቀ ስለሆነ ወደ ህግ ቀርቦ በአግባቡ
አልተጠየቀም ሲሉ የከተማዋ ኗሪዎች ያማርራሉ፣