Sunday, May 25, 2014

በደቡብ ኢትዮጲያ ኦሞ ሽምጥ ሸለቆ በጂንካ ወረዳ አከባቢ ለሚገኙ አርሶ አደሮች ግንቦት12/2006ዓ/ም ፖሊስ ከቀያቸው በሃይል ሊያፈናቅላቸው በሞከሩበት ግዜ በተከሰተ ግጭት የመቶ ሰው ህይወት እንደጠፋ ታወቀ።



በመረጃው መሰረት የወያኔ ኢህአደግ መሪዎች በኦሞ ሽምጥ ሸለቆ አካባቢ ለሚኖሩ ዜጎቻችን መሬታቸው ለስዃር ፋብሪካ መስርያ በሚል ሰበብ ፖሊስ በመላክ በሃይል ሊያፈናቅልዋቸው በጀመሩበት ግዜ የአከባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው ቅያችንን አሳልፈን አንሰጥም በማለት በተከሰተ ሃይል የተሞላበት ግጭት  80 የሚሆኑት ንፁሃን ዜጎቻችን ሲሞቱ ከስርአቱ አጫፋሪ ከሆኑት የፖሊስ አባላት ደግሞ 20 እንደተገደሉ ለማወቅ ተችለዋል።
   በተጨማሪም በህዝቡና በፖሊሶች መካከል የተነሳው ግጭት ሊቆም ባለመቻሉ ምክንያት የሰጉ የአካባቢው አስተዳዳሪዎች  ከሃዋሳ ከተማ የአግአዚ ኮማንዶ ሬጅመንት ልከው በህዝቡ ላይ ከባድ ጭካኔ የተሞላበት ድብደባና እስራት ስላወረዱባቸው በዚህ ምክንያት ነዋሪዎቹ  ከባድ ብረት ከታጠቁት ወታደሮች ጋር ውጊያ ለመክፈት አቅም ስላአጠራቸው ህፃናትና ሽማግሊዎች የሚገኙባቸው የአከባቢው ነዋሪዎች መኖሪያ ቤታቸውን ዘግተው እግራቸው ወደ አማራቸው እየጠፉ መሆነቸው ሊታወቅ ታችለዋል።
  በተመሳሳይ በኢንቨስትመንት ስም በሁሉም የአገራችን አከባቢዎች በስዃር ፋብሪካ ስም እየተደረገ ያለው የመሬት ወረራና አርሶአደሮችን በጅምላ የማፈናቀል ሂደት በሕወሓት ኢህአዴግ እየተፈጸመ ያለ ሃላፊነት የጎደለው ተግባር መሆኑን በተለያዩ ግዜ በዜና እወጃችን ስንገልፅ መቆየታችን ይታወሳል።