Sunday, May 25, 2014

በአማራ ክልል የሚገኙ የቅማንት ብሄርሰብ በብሄራችን እንድንተዳደር መብታችን ይከበር በማለት ግንቦት 3/ 2006 ዓ.ም የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳካሄዱ ተገለፀ።



ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ መሰረት እነዚህ በአማራ ክልል የሚኖሩ የቅማንት ብሄረሰብ እርስ በራሳችን መተዳደር አለብን በማለት በተደጋጋሚ ወደ ክልሉ ምክር ቤት አቤቱታቸውን ሲያቀርቡ የቆዩ ቢሆኑም፣ የሚሰማቸው የመንግስት አካል ባለማግኘታቸው ግንቦት 3/2006 ዓ.ም በጎንደር ከተማ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳካሄዱ ታወቀ።
መረጃው ጨምሮ እንደሚያስረዳው የወያኔ ኢህአዴግ አፋኝ ስርዓት የነበረውን የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለመበተን እንደልማዱ ተላላኪዎቹ ወሮ በላ ፖሊሶች አሰማርቶ ሰልፉን ለመበተን በሞከረበት ግዜ ህዝቡ መሳርያ ከታጠቁት ፖሊሶች ጋር በደንጋይና በዱላ በመግጠም በከተማዋ ከባድ ግጭት ተፈጥሮ እንደነበር ሊታወቅ ተችሏል።
የመብት ጥያቄ ባነሱት በቅማንት ብሄረሰብ ሰልፈኞችና በስርዓቱ ፖሊስ መካከል በተፈጠረው ከባድ ግጭት ከቅማንት ብሄረሰብ 7 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ሰልፉን ለመበተንና ለመጨፍጨፍ ከመጡት ተላላኪ የስርዓቱ ፖሊሶች ደግሞ 3 እንደተገደሉ ግጭቱም እስካሁን ሊረጋጋ እንዳልቻለ ታውቋል።