Sunday, May 25, 2014

በሰሜን ዕዝ የሚገኙ ወታደሮች በተደጋጋሚ ሲያካይዱት የቆዩት ከውትድርና አሰናብቱን የሚል ተቃውሞ ወደ ከፋ ሁኒታ እንዳይሸጋገር የሰጉ የወያኔ ኢህአደግ መሪዎች ለይስሙላና ለማረጋጋት ብለው ጥቂት ወታደሮችን እንደሸኙ ታወቀ።



 በመረጃው መሰረት በሰሜናዊ ምስራቅ ዕዝ በ25ኛ ክፍለ-ጦር ሰራዊት የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከውትድርና ሸኙን የሚሉ ተቃውሞዎችን ለማረጋጋት ሲሉ ከአንድ ሬጅመንት ከ60 እስከ 70 የሚሆኑ ወታደሮችን እየሸኝዋቸው እንዳሉ ለማወቅ ተችለዋል።
    በማስከተል እነኚህ በ25ኛ ክፍለ-ጦር የሚገኙ ወታደሮች በፊናቸው ስርአቱ እያደረገ ባለው ተግባር ደስተኞች አለመሆናቸውን ሲገልፁ “ ይህ ለኛ ለማታለልና ለይስሙላ ያደርጋችሁት እንጂ ጥያቅያችን ሰምታችሁ የመለሳችሁልን አይደለም። በዚህ መሰረት ደግሞ የምታሰናቡቱት ያላችሁት የሰራዊት ብዛትና ጥያቄ ካቀረበው ጋር የሚመመጣጠን አይደለም በጣም ትንሽ ነው፣ እያሏቸው እንዳሉና በዚህ መሰረትም ጥያቄዎቻቸው ያልተመለሰላቸው የሰራዊቱ አባላት አሁንም አሰናቡትን እያሉ ተቃውሞያቸውን እየቀጠሉ እንዳሉ መረጃው አክሎ አስረድተዋል።