ከመከላከያ ሰራዊት ውስጥ
አፈትልኮ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው ግንቦት 7 2006 ዓ/ም በ21ኛ ክፍለጦር 7ኛ ሬጅመንት 2ኛ ሃይል በባዳ ግንባር ልዩ
ስሙ ምስሊ በሚባል ቦታ አሰናብቱን በሚል ጥያቄ
ምክንያት በሃይሉ ውስጥ በተፈጠረ ግጭት የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆነው ወታደር በላይነህ አለሙ ሲሞት አንድ ስሙ ለጊዜው ያልታወቀ ከወላይታ ብሄር ደግሞ በከባድ ቆስሎ ሆስፒታል እንደሚገኝ ታውቋል።
በተመሳሳይ በባዳ ግንባር ልዩ ስሙ አዲ ኩማ በሚባል ቦታ በአንድ ክፍለጦር የስለያ አባል የነበረ የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ አስር አለቃ
በቀለ ድጉማ በተደጋጋሚ አሰናብቱኝ የሚል ጥያቄ በሚያቀርብበት ሰዓት ሊመሰልለት ባለመቻሉና የትዳር አጋሩን በአንድ የሰራዊት አዛዥ
ስለተደፈረች ክስ አቅርቦ ተገቢ መልስ ባለማግኘቱ ምክንያት ህይወቱን በራሱ እጅ ለማጥፋት እንደተገደደ የደረሰን መረጃ አስረድቷል።