Thursday, May 29, 2014

በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ኢሮብ ወረዳ ደውሃን ከተማ ደውሃን አካባቢ የሚገኝ ህዝብ በወያኔ ኢ.ህ.አ.ደ.ግ ወታደሮች በላያቸው ላይ እየወረደ ያለው በደልና ግፍ እንዲቆም ተቃውሞ እያሰሙ እንዳሉ ከአከባቢው የደረሰን መረጃ አመለከተ።



የኢሮብ ወረዳ ሰብዓ ሓራዛ ቀበሌ የሰብዓታ አከባቢ ህዝብ በአካባቢው የሚገኙ የ11ኛ ክፍለ ጦር በወያኔ ኢ.ህ.አ.ደ.ግ ወታደሮች እየተገደሉ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው በወታደሮች ከተገደሉት አንዱ ወጣት ዳኒኤል አሰፋ ገብራይ ሲሆን ግንቦት 6/2006ዓ/ም በወይዘሮ ትርሓስ መኖሪያ ቤት በአራት ወታደሮች ተደብድቦ ሂወቱ እንዳለፈ ታውቋል።
መረጃው በማስከተልም በኢሮብ ወረዳ ባለፉት ስድስት አመታት ከስምንት በላይ ንፁሃን ዜጎቻችን በወያኔ ወታደሮች እንደተገደሉ ከገለፀ በኋላ በተፈፀመው ግድያ የኢሮብ ወረዳ ህዝብ በላያቸው ላይ እየወረደ ያለው ግፍ እንዲቆም በማለት በአካባቢው የሚገኙ ወታደሮችን ከአካባቢው እንዲወጡ የሚጎተጉት ተቃውሞ እንዳካሄዱ ለማወቅ ተችሏል።
   በኢሮብ ወረዳ ህዝብ የተነሳው ተቃውሞ የሰጉ የምስራቃዊ ዞን ፀጥታ ሃላፊ አቶ ዊንታ ተክሉ ከባልደረቦቹ ከነገብረ ካሕሳይ ጋር በመሆን ህዝቡን ለማረጋጋትና ለማታለል ሲል “ የሆነ ወታደር ወደ ደውሃን ከተማ እንዳይገባ ክልክለናል ሲሉ መናገራቸው መረጃው አክሎ አስረድተዋል።