Sunday, May 25, 2014

በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ኢሮብ ወረዳ በሁሉም ቀበሌዎች የሚገኙ የስርዓቱ ካድሬዎች በጉቦና በስርቆት ተግባር ላይ ስለተሰማሩ የወረዳዋ ነዋሪ ህዝብ ምሬቱን እያሰማ እንደሚገኝ ተወቀ።



   ምንጮቻችን በላኩት መረጃ መሰረት በኢሮብ ወረዳ የሚገኙ የስርዓቱ ካድሬዎች የሃገርንና የህዝብን ሃብት በማጥፋፋት ስራ እንደተሰማሩ በመግለጽ የህዝቡ ምሬት ያሰጋቸው የወረዳዋ አስተዳዳሪዎች ደግሞ ለማስመሰልና ህዝብን ለማታለል ከግንቦት 9 እስከ 14 ተከታታይ ስብሰባ እንዳካሄዱ ታውቋል።
የሃገርንና የህዝብን ገንዘብ የማጠፋፋት ሂደት የሚመለከት በከፍተኛ የወረዳዋ አስተዳዳሪዎች እየተካሄደ ያለው ስብሰባ አሁንም እየቀጠለ እንደሚገኝ የገለፀው መረጃው በስርቆትና በማጥፋፋት ተግባር ላይ እጅ አላቸው ከተባሉት የወረዳዋ ካድሬዎች መካከል
1.   ስዩም ዑሞር
2.   ዓዲ ዑመር ወሉ
3.   በርሀ ሓጎስ
4.   ንጉስ አብረሃ የተባሉት የሚገኝባቸው ሲሆኑ ስብሰባውን እየመራ ያለው ዓዲ ዑሞር ወሉ እራሱ በዚህ ተግባር የተሰማራ ሲሆን ግምገማውን የሚከታተሉት ደግሞ የኢሮብ ወረዳ የወጣቶች ሊቀመንበር ወዲ ካሕሳይ የወረዳዋ አፈ ጉባኤ ንጉስ ካሕሳይ፤የወረዳዋ የፀጥታ ሓላፊ ወለ ግርጊስ  መሃሪ፤ የወረዳዋ አቃቢ ህግ ዳዊት የተባሉ የስርዓቱ ካድሬዎች እንደሆኑ ምንጮቻችን አስታውቀዋል።