Sunday, May 25, 2014

በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ኢሮብ ወረዳ ዓገረለኹማ ቀበሌ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች ለተቸገሩ ወጎኖቻችን ተብሎ የተላከ እርዳታ ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት እንዳሉ ታወቀ።



በመረጃው መሰረት በኢሮብ ወረዳ ዓገረለኹማ ቀበሌ የሚገኙ አስተዳደሮች ከለጋሾች ለድሃ ህዝብ ተብሎ የተላከውን እህል እያጠፋፉት መሆናቸውን ከገለፀ በኋላ እያጠፋፉት ካሉ አስተዳደሮች ድግሞ አቶ አለማና ምክትሉ ተስፉ እንደሆኑ በመግለፅ ህዝቡ ታባብሮ ህግ ፊት ቢያቀርባቸውም ዳኞቹ ግን የአጥፊዎቹ ተባባሪ ሰለሆኑ ለማስመሰል ብለው ለአንድ ወር አስረው እንደለቀቅዋቸው ለማወቅ ተችሏል።
    በተመሳሳይም ከኢሮብ ወረዳ ሳንወጣ የሓራዛ ሰብዓታ ፕሮፓጋንዳ ሃላፊ የሆነው አቶ ዮውሃንስ ዑመርና ምክትሉ ፍስሃየ መድሃንየ የተሰጣቸውን ስልጣን ተጠቅመው የህዝብ ንብረት በማጠፋፋትና ጉቦ በመቀበል ላይ ተሰማርተው መገኘታቸው ተረጋግጦ እያለ ከአንድ ወር ያልበለጠ ግዜ ታስረው ወደ ስራቸው እንደተመለሱ መረጃው አክሎ አስረድቷል።