Friday, August 1, 2014

የህወሓት ኢህአዴግ ባለስልጣናት ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ትገናኛላችሁ በሚል ምክንያት ሐምሌ 17/2006/ዓ.ም በመቐለ ከተማ ንፁሃን ወጣቶችን እንዳሰሯቸው ምንጮቻችን ከከተማዋ ገለፁ፣፣



    የወያኔ ኢህአዴግ ስርዓት በ2007 ዓ,ም ለሚያካሄደው የይስሙላ ምርጫ በተቃዋሚ ድርጅቶች እንዳይሸነፍ በከባድ ስጋት ላይ ወድቆ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ገልፀው እየተካሄደ ላለው ህዝባዊ ተቃውሞ ‘ለመግታትና ለመቆጣጠር ወደ ሁሉም የሃገራችን አካባቢዎች በተለይ ደግሞ ወደ ከተሞች ወታደሮች፤ ፖሊሶችና የደህንነት አባላቶቹን በማሰማራት ያሰጉኛል ያላቸውን ንፁሃን ወጣቶች በጥርጣሬ እየያዘ ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ትገናኛላችሁ  በሚል ታማኝነት በሌለው ጥርጣሬ በጅምላ በማሰር ላይ ተጠምዶ እንደሚገኝ የተገኘው መረጃ አስታወቀ፣፣
     ምንም አይነት ወንጀል ሳይኖራቸው ከታሰሩት ንፁሃን ወጣት ተማሪዎች የተወሰኑትን ለመጥቀስ፣- ምስጋናው ተካልኝ፤ ፀጋይ ምሕረታአብና ሻሸመኔ በሚል ቅጥያ ስም የሚታወቅ የሚገኝባቸው በርከት ያሉ ዜጎቻችን መታሰራቸውን መረጃው ጨምረው አስታውቀዋል፣፣