Friday, August 1, 2014

በመቐለ ከተማ በእንዳሚካኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ የሚገኙ ቤቶች ይፈርሳሉ ተብለው ፕላን ስለወጣላቸው የአካባቢው ህብረተሰብ ተለዋጭ መሬት ስላልተሰጣቸው በከባድ ጭንቀት ላይ እንደሚገኙ ታወቀ፣፣



በመቐለ ከተማ መንገድ ለማስተካከል በሚል ስም እንዲፈርሱ ፕላን የወጣላቸው መኖርያ ቤቶች የአካባቢው ህዝብ ያለምንም ቅድመ ዝግጅት ሳያደርግና  ተለዋጭ መሬት ሳይሰጠው  እየተተገበረ በመሆኑ ነዋሪዎቹ በከባድ ችግር ውስጥ ወድቀው እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገለፁ፣፣
    የእንዳሚካኤል አካባቢ ህዝብ አጋጥሟቸው ባለው ችግር ምክንያት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አስበው የነበሩ ቢሆኑም የህወሓት ማሌሊት ባለስልጣናት ግን ከዚህ በፊት በአላማጣ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ‘ለማድረግ በወጣ ህዝብ ላይ ያስከተሉት ጭፍጨፋ በኛም ይደግሙታል ዋስትና የለንም በማለት በከባድ ጭንቀት ውስጥ እንደሚገኙ ለማወቅ ትችሏል፣፣
   ህዝቡ በአደባባይ ወጥቶ በሰላማዊ ሰልፍ ተቃውሞውን እንዳይገልፅ እድል ስላጣ ይፋ ባልሆነ መንገድ ስሜቱን በመግለፅ ላይ እንደሚገኝ ምንጮቻችን አክለው አስታውቀዋል፣፣