ውስጥ አዋቂዎች መሰረት
አድርጎ ከመቐለ ከተማ የደርሰን መረጃ እንደገለጸው የህወሓት ኢህአዴግ ባለስልጣናት “የትግራይ ዲያስፖራ ፌስቲቫል “ በሚል ስም
በተለያዩ ሃገራት ተሰድደው ለሚኖሩ የትግራይ ታወላጆች ጥሪ አድርገው እዩሉን ስምሉን ለማለትና በሱ አድርገው የፖለቲካ ጥቅም ለማግኘት
እያደረጉት ያለው ሽርጉድ፣ ለትግራይ ክልል ልማታዊ ስራዎች ተብሎ ወጪ ከተደረገ ከፍተኛ ገንዘብ መሆኑን የተገኘው መረጃ አስታወቀ፣፣
ይህ ከሃምሌ 24 እስከ 30 /2006ዓ/ም “በትግራይ ተወላጆች ዲያስፖራ
ፌስቲቫል “ ስም በመቐለ ከተማ ለማካሄድ እንደ አንድ ትልቅ አጀንዳ ይዘው በሙሉ አቅማቸው ለመፈፀም እየተንቀሳቀሱለት ያለው ለህዝብና
ለሃገር ጥቅም ግምት ውስጥ ያላስገባው ፌስቲቫል አላማው የመቐለ ከተማ ጎደናዎች እንዲያሸበርቁ በማድረግ ከውጭ ለመጡት ዲያስፖራ
በህወሓት ኢህአዴግ ስርአት ትግራይ እንደለማች አስመስለህ ለማቅረብ ያለመ እንደሆነ ለማወቅ ተችለዋል፣፣
ይህ ያልሆነውን ምስል ለመያዝ ተብሎ ከልክ ያለፈው ወጭ የተደረገበት
ዝግጅት የትግራይ ጭቁኑ ህዝብ በተለያዩ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እጦት በከባድ ችግር እየተሰቃየ ባለበት ወቅት ይህን ያክል ወጪ
እንዲወጣ መደረጉ ትክክል አይደለም በማለት የመቐለ ከተማ ህዝብ እየተነጋገረበት እንደሆነ መረጃው አክሎ አስረድተዋል፣፣