Tuesday, August 5, 2014

የህዝቡን ንሮ የማያሻሽል ልማት ውጤት የለውም!



ልማትን ማረጋገጥ ለአንድ አገርም ይሁን መንግስት አስፈላጊ ነው ብቻ ሳይሆን ዋናውና መሰረታዊ የግንባት መነሻ ነው ተብሎ የሚገለፅበት ምክንያት ካለ ልማት ምንም አይነት ጥንካሬ ስለ ማይረጋገጥ ነው።
    ልማትና አገራዊ እድገት መሰረቱ በዋናነት ባገሪቱ ውስጥ  ዴሞክራሲያዊ ስርአት ሲኖርና ለሚዘጋጀው የልማት ፕሮግራም የሚያስፈፅም ቀና የሆነ አስተሳሰብና ሲኖር እንደሆነ የሚታወቅ ቢሆንም። በየግዜው በሚመጡ ስርአቶችና እነሱን ተከትለው በሚወጡ ፀረ ህዝብ ፖሊስዎች ግን። አገራችን ከኃላ ቀርነትና ከድህነት በስተቀር። በእድገትና ግስጋሴ መታወቅ አልቻለችም።
     የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት ነጋ ጠባ በተመዘገቡ የልማት ፕሮግራምና ፈታን ኤኮኖሚ አስመልክተው ከ10 አመታት በላይ ለኢትዮጵያ ህዝብና የአለም ማህበረሰብ ሲያደናግሩ ቢቆይም ገነባነው በሚሉት ኢንዳስትሪና አስመዘገብነው ብለው በሚመኩበት የኢኮኖሚ እድገት ከስርአቱ በለስልጣኖችና ካድሬዎቻቸው በስተቀር የአብዛኛው ድሃ ህብረተሰብ ማህበራዊ ሂወት ሲቀይር አልተስተዋለም።
     የህወሃት ባለስልጣኖች የትግራይ ህዝብ ሃብት ናቸው ብለው በሚገልፅዋቸው የትእምት ድርጅቶች ስም እየነገዱ ከነሱ በሚገኘው በሚልዮን የሚገመት ገንዘብ ባለቢላዎችና ባለ ዘመናዊ መኪናዎች ለመሆን በቅቷል፣ የድርጅቱ ባለቤት እንደሆነ የሚቀለድበት ጭቁኑ ህብረተሰብ ግን ንሮውን ከእጅ ወደ አፍ ሆነበት መጨረሻ በሌለው የድህነት ዓዘቕት ውስጥ ተዘፍቆ እንደሚገኝ ምስክር የሚያስፈልገው አይደለም።
    የትግራይ ክልል ባለስልጣኖች እነሱ በሚቆጣጠሯቸው የተለያዩ የሚድያ መስርያዎቻቸው ተጠቅመው እያስተዋወቁት የሰነበቱትና ባለፈው ሳምንት በመቀሌ ከተማ ያካሄዱትን አለም አቀፍ የትግራይ ዲያስፖራ ፌስትቫል አላማው ለምን እንደነበር በግልፅ የሚታወቅ ነው።
     ያገር ልማት ባገሩ ተወላጅ የሚል አስተሳሰብ እምብዛም የማያደናግር የተቀደሰ አባባል ቢሆንም ይህ በአንባገነኖች የህወሃት ባለስልጣኖች እየተካሄደ ያለውን ፌስቲቫል የድሃው ወገን ጥቅም ማረጋገጥ ይቻላል ብሎ ማሰብ ግን የሚታሰብ አይደለም።
    አንዳንድ የዋሆችና የዲያስፖራ ወገኖች በጦርነት የተጎሳቆለች ትግራይን ለመገንባት፤ የበለፀገች አገርና ከድህነት የተላቀቀ ህዝብ እንዲኖር በመለት። ገንዘባቸውና እውቀታቸውን አሰማርተው ራሳቸውና ህብረተሰቡን ለመጥቀም በሚል የተቀደሰ ተግባር ቀደም ሲል አንዳንድ ተወላጆች ለጀመሩት በጎ እንቅስቃሴ በስፋት እንዲጠቀሙበት ብለው በማሰብ ወደ አገራቸው ቢገቡም ያሰቡትን እቅድ ተሳክቶ ወደ ስራ እስኪሰማሩ ድረስ የነበረውን የቢሮክራሲ ችግሮች ምን ያህል አሰልቺና አስቸጋሪ እንደነበረ፤ ለዚሁ ሁሉ ውጣ ውረድ አልፈው ይብዛም ይነስም ድርጅቶች ካቓቓሙ በኃላም፤ ምርታቸው የድሃው ህዝብ ንሮ የሚለውጡ ሳይሆን የስርኣቱን ዕዲሜ ለመራዘምና የመሪዎችና የካድሬዎቹ ካዝና ለሞምላት የሚደረግ ውጣ ውረድ እነደሆነ። ለማንም የሚሰወር አይሆንም።
     የህወሃት ኢህአዴግ መሬዎች ቀድመው መተግበር የሚገባቸውን የልማት ፕሮግራም ወደኃላ በማምጣት ህዝቡን ሊያደናግሩት ማሰባቸው እምብዛም የሚያስገርም አይደለም፣ በኢንቨስትመንትና ባገር ልማት ስም ሰፋፊ ለእርሻ ስራ የሚውሉ ለም መሬቶች ለውጭ ባለ ሃብቶች እስከ 100 አመት በሚደርስ በኪራይ መልክ አሳልፈው ከመስጠት ይልቅ በቅድምያ በተለያዩ አለማት ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ባለ ሃብቶች መስጠት በተገባቸው፣ ጅብ ከሄደ ውሻ ይጮኃል እንደሚባለው ማለቅያ የሌለው ያገሪትዋ ሃብት በባእድ ባለሃብቶች እንዲወረር ከተደረገ በኃላ የዲያስፖራ ፌስቲቫል አስመልክቶ የሚካሄደው አስመሳይ ፕሮፖጋንዳ ትርጉም የሚሰጠው አይደለም።
    ባለፉት አመታት በጋንቤላ አካባቢና ሌሎች አካባቢዎች ለውጭ ባለ ሃብቶች አሳልፎው የሰጡትን ሰፋፊ ለም መሬቶችና ሌሎች ያገሪትዎ አንጡራ ሃብቶች ባገራችን ባለሃብቶች መሰራት ሲገባው ሃላፊነት በጎደሎው መንገድ ከፍተኛ ወንጀል ተፈፅመዋል በማለት እንዳንድ ስለ አገራችን ሁኔታ ይመለከተናል የሚሉ የተቃዋሚ ድርጅቶችና ህዝቡ በጥብቅ ማውግውዛቸው የሚታወቅ ሆኖ ይህ ቀደም ብሎ የተፈፀመውን ታሪካው ስህተት ገና ካሁን በኃላም እንዲፈፅሙት እየተዘጋጁበት ያለውን አገር የማፈራረስ ወንጀል ለማድበስበስ ብለው አሁንም የመቀሌና የኣካባቢዋ የሚኖርበትና ህወቱን የሚመራበት የነበረ መሬት በመቀማት  ለዲያስፖራዎች ወገኖች በመስጠት ከፖለቲካዊ ውድቀት ለመዳን ብለው  እንጂ አገሪቱ ለመጥቀም የታሰበ እንዳልሆነ መታወቅ ይገባል።