Thursday, August 7, 2014

በሰሜን ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ አብራጂራ አካባቢ የሚገኙ የወያኔ ኢ,ህ,አ.ዴ.ግ ተላላኪ ኢንቨስተሮች የቀን ሰራተኛውን ጉልበትና ህይወት እየበዘበዙ መሆናቸውን ምንጮቻችን አስረድተዋል።



መተማ ወረዳ አብራጅራ አካባቢ ደለሎ ቁጥር አንድ በተባለው የእርሻ ስራ ድርጅት የገዥው መንግስት ተላላኪ ካድሬዎች በኢንቨስትመንት ስም ተደራጅተው ደሃ የቀን ሰራተኞችን አሰርተው ያለምንም ክፍያ ደብድበው እያባረሯቸው እንደሆኑና በሰራተኞች መካከልም የብሄር ልዩነት በመፍጠር እርስ በራሳቸው እንዲጋጩ በማድረግ የሁመራና የቋራ ተወላጅ የቀን ሰራተኞችን ለሞት እንዲጋለጡ ምክንያት እንደሆነ መረጃው ገልጸዋል።
    የገዥው ፓርቲ ታጣቂ አባላት ግጭቱን ለማርገብ በሚል ምክንያት በመካከል ገብተው የሟቾችን ህይወት እንደቀጠፉም መርጃው አክሎ አስረድተዋል።