በመቐለ አካባቢ የሚኖሩ
አርሶ አደሮች መሬታችሁ በጥሩ ሁኔታ አልያዛችሁትም የልማት ኣርበኛ አርሶ-አደር አልሆናችሁም በሚል ተጨባጭነት በሌለው ምክንያት
አስተዳዳሪዎቹ የእርሻ መሬታቸውን ያለ ምንም ካሳና ተለዋጭ መሬት
እየቀሙ የተለያዩ ጥቅማጥቅም ለሚሰጣቸው ባለሃብት እያደሉት መሆናቸውን ታውቋል፣፣
መረጃው ጨምሮ እንደገለፀው የመቐለ ከተማ አካባቢ ነዋሪ ህዝብ ይህን በገዥው
መንግስት ባለስልጣን አማካኝነት በአርሶ አደሮች ላይ እየተፈፀመ ያለው መሬት እየቀማህ ለባለሃብቶች መስጠት ትክክል አይደለም አርሶ
አደሮች ቤተሰባቸውን በምን ሊያስተዳድሩ ነው እንዲህ አይነት እርምጃ እየተወሰደ ያለው ሲሉ ምሬታቸውን እየገለፁ መሆናቸውን ለማወቅ
ተችሏል፣፣